ዓርብ 11 ማርች 2022

ወግ

ኑሮ ለማሸነፍ

አጭር ልብወለድ

በንግድ ሥራ መተዳደር ከጀመርኩኝ እነሆ አሥር ዓመት አለፈኝ ፤ ኑሮ ለማሸነፍ ጥሬ ግሬ ለመኖር ታትሬ እሠራለሁ፡፡ ነግጄ ለማትረፍ ከትንሽ እስከ ቀላል የተባሉትን ሥራዎች ሁሉ ሠርቻለሁ፡፡ ከመንግስት፣ ከጓደኛ፣ ከቤተሰብ ልዩ ልዩ ብድሮችን በመውሰድ የንግድ ሥራዬን ለማፋጠን ያደረኩት ሙከራም መክል፡፡ ጉዳዩ የችሎታ ማነስ ነው እንዳልል፤ እኔ ሀሳብ የለገስኳቸው ሰዎች ከእኔ በተሻለ ሠርተው ተለውጠዋል፤ ዕጣ ፋንታ እንዳልል የሚገርሙ መልካም የሥራ አጋጣሚዎችን ማግኘት የተነሳ ዕድለኛ እንደሆንኩኝ ሰዎች ይነግሩኛል፡፡ ሠራቼ የማገኘው ገንዘብ መቅኖ አጥቶ ባክኖ ይቀራል፡፡ ተጠራቅሞ ቅርስ ሊሆነኝ ሲገባው እጄ ሳይገባ ሳልቆጥረው በልዩ ልዩ አጋጣሚዎች ተሰናብቶኝ ሄዳል፡፡ ያገኘኋቸው ብዙ ጥሩ እና አጎጊ ሥራዎች ሠርቼ ውጤት ላይ ሳይደርስ መሀል ላይ ተሰናክለው ይቀራሉ፡፡ ገንዘብን አላባክንም ሱስ የለብኝም፤ ተግቼ እሠራለሁ ግን ሥራዬ መቅኖ የሌለው እርባናቢስ ነው፡፡

ቤተሰቦቼ፣ ባልንጀሮቼ በሁኔታው በመገረም ደግሞም መቸገሬ እና መጎዳቴ ቢያሳስባቸው የየራሳቸውን ምክር ይሰጡኛል፡፡ በተደጋጋሚ ሥራ አልሳካ ማለቱን የተመለከቱት ለምን ለባለስልጣናት መማለጃ (ጉቦ) በመስጠት አትራም ሲሉ፤የመኪና መለዋወጫ ሱቅ ገበያ መቀዝቀዙን የተመለከቱት ደግሞ አዋቂ (ጠንቋይ) ዘንድ ሄደህ መፍትሄ ፈልግ ብለው ይጠቁመኛል፡፡ እኔ ግን የእነርሱን ምክር ለመቀበል ልቦናዬ ሃይማኖቴም አልፈቀደም፡፡ ምርጫዬ እግዚአብሔር ሆነ ዘወት ተስፋ አደርገዋለው፤ እመካበታለሁም፡፡

 በክርስትና ሕይወቴ ትጉህ አይደለሁም፤ብቻ በሥጋዊ ኑሮዬ ሥኬትን አለማግኘት እና መቸገር ስለሚያበሳጨኝ እግዚአብሔርን አማርረዋለሁ፤ ደግሜ ደጋግሜ አማርራለሁ እነጫነጫለሁ እበሳጫለሁ በጥቅሉ ደስተኛ አይደለሁም ፡፡ ከመኖሪያ ቤቴ አጠገብ የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስያን አለ፡፡ ጠዋት ወደ ሥራ ስሄድ ቤተ ክርስቲያን ገብቼ በአጭሩ በሰላም ያሳደርከኝ በሰላም አውለኝ ብዬ ሦስቴ ከአንገቴ ጎንበስ ጎንበስ ብዬ በሩን ተሳልሜ ያባረሩኝ ይመስል በፍጥነት እሄዳለሁ፡፡ የሚገርመኝ ደግሞ ምንም የምቸኩሉበት የሚያጣድፍ ጉዳይ አለመኖሩ ነው፡፡ ውስጤን የሚያብከነክነኝን የኑሮዬን ጉዳይ አንስቼ ጸልዬ አላውቅም፡፡ ነገርግን ከቅዱስ ሚካኤል ጋር የተለየ ቁርኝት አለኝ ልደቴ፣ ታምሜ የዳንኩበት፣ መጀመሪያ ሥራ የያዝኩበት ቀን የሚካኤል ቀን ነው፡፡ በዕለቱ ቤተክርስቲያን ደርሼ ጸሎት አድርጌ ወደ ጉዳዮ ካልሄድኩ ባጣ ባጣ ቃሪያ ጥፊዮን ቀምሼ እውላለሁ፡፡ ስለዚህ የተለየ አክብሮት እና ፍቅር አለኝ ፡፡ በአብዛኛውን የቅዱስ ሚካኤል ቀን በእለተ ቀኑ ሥራ ሳልሰራ አከብረዋለሁ፡፡

ቅዳሜ ኪሴ ባዶ ሆኖ ቡዙ ባለእዳዎቼ አይናቸውን አፍጥጠው መጥተውብኝ የምከፍለው አጥቼ ተጨንቄአለሁ ይባስ ብሎ ደግሞ ለሠራተኞች የምከፍለው ብር በማጣቴ በጣም ተበሳጭቼ ግራገብቶኛል፡፡ ቅዳሜ አመሻሽ ድረስ ስልኬን አጥፍቼ ከሥራ ቦታዬ ተደብቄ ቆየሁ፡፡ በማግስቱ እሁድ የቅዱስ ሚካኤል ቀን መሆኑን ሳውቅ መረጋጋት እና ደስታ ተሰማኝ፡፡ ሌሊቱን ሁሉ በሀሳቡ ማዕበል ስናወጽ እንቅልፍ አጥቼ አደርኩ፡፡ እሁድ ዕለት ሲነጋጋ ከመኝታዬ ተነስቼ ነጠላዬን አጣፍቼ ኪዳን ለማድረስ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄድኩ፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ ውስጥ ገባሁ ሥርዓተ ቅዳሴውን በተመሰጦ አስቀደስኩ፡፡ ከወተሮው የበለጠ መንፈሳዊ ደስታ እና ብርታት ውስጤ ዘልቆ ሲገባ ይሰማኛል፡፡ ሌሊቱን ሁሉ በጣም ተከፍቼ በማደሬ የሆዴን ብሶት ሁሉ ለቅዱስ ሚካኤል በጸሎት መንገር ጀመርኩኝ፡፡ እንባዬ ምንጣፍን እያራሰው ሰውነቴ እስኪዝል ድረስ የልቤን ሀዘን የሆነውን የዕለት እንጀራዬን ኑሮዬን ስለማስተካከል ልመናዬን በጽኑ ዕምነት አቀረብኩኝ፡፡

ቅዳሴ ሥርዓቱ አልቆ ውስጥ ያላችሁ እና በዙሪያው የምትገኙ ሁሉ በዓውደ ምህረቱ ላይ ትምህርት ስለሚሰጥ ፊት ለፊት ወንበር ላይ ተቀመጡ ሲባል እየሰማሁ ብቻ ራሴን ወንበር ላይ ተመቻችቼ ተቀምጬ አገኘሁት፡፡ መምህሩ እንዲህ ብሎ ማስተማር ጀመረ “እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ፥ የምድርን በረከት ትበላላችሁ” ኢሳ.1፥19 እግዚአብሔርን እሺ በማለት መታዘዛችን የሚገለጠው ሕጉን እና ትዕዛዙን አክብረን በመፈጸም ነው፡፡ ኑሮአችን እንዲባረክ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሆነውን አሥራቱን፣ በኩራቱን፣ ቀዳሚቱን ማውጣት አለብን እያለ ማስተማሩን ቀጠለ ውኃ እንደጠማው ሰው ቃሉ ወደ ውስጤ ጅው ብሎ ቁርቁር እያለ ሲገባ ይታየኛል፡፡

መምህሩ ማስተማሩን እንዲህ እያለ ማስተማሩን ቀጠለ በቡሉይ ኪዳን ነቢዩ ለእግዚአብሔር ቤት በሚሠጠው በኩራት በረከት እንደሚሰጥ እንዲህ እያለ ያስረዳል “የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የዱቄታችሁን በኵራት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ።” ቡሏል፡፡/ትን. ሕዝ. 44፥30/ ብዙዎቻችን የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር ሳንሰጥ በረከት ማግኘት እንፈልጋለን ነገርግን መጀመሪያ መቅደም ያለበት እሺ ብሎ መታዘዝ ነው ብሎ አስተማረ መምህሩ የሚናገረው የእግዚአብሔር ቃል እኔን እያፈራረሰ የሚጠግነኝ አዲስ ቅርጽ የሚሰጠኝ እየመሰለኝ መላ ሰውነቴን ወረረው ፡፡

በዓውደ ምህረቱ ላይ የሚሰጠው ትምህርት በጣም ውሳጣዊ ሰውነቴን እየሠረሰረ ገብል ከመመሰጤ የተነሳም ከሌላው ሰው የበለጠ ጮክ እያልኩኝ አሜን አሜን እል ነበር፡፡ መምህሩም ትምህርቱን ቀጥሎ እንዲህ አለ “አሁንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ። ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ።” ትንቢተ. ሐጌ.1፥5-6 በማለት በሰፊው ትምህርቱን ሰጠ፡፡

መምህሩ ሲያስተምር ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ እያለ ሲናገር መንገዴና ልቤ የተዘበራረቀብኝ መሆኑን ተረዳሁ እንዲያውም እኔን የሚያውቀኝ ይመስል ሁሉም የሚናገረው ቃል በሙሉ የእኔን ሕይወት የሚመለከት የሚወቅስ ነር፡፡ በተለይ ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ይመስላል የሚለው ቃል ልቤን ሰበረው፡፡ ትምህርቱ ተጠናቀቀ እኔ ግን ፈዝዤ ቀረሁ ምን ላድርግ ? ምን ልሁን አልኩኘ ?

 ከትምህርቱ በኋላ ስረጋጋ ቆም ብዬ እኔ ማነኝ ቤቴስ ምንድን ነው ? ቡዬ ራሴን ጠየኩኝ ራሴን መረመርኩት መንፈሳዊ ሂወቴን ፈተሽኩኝ፡፡ ከቀናት ጽሞና በኋላ አንድ ነገር ተረዳሁ መንፈሳዊ ሕይወቴ ሲስተካከል እና ለእግዚአብሔር ስታዘዝ የዚህን ዓለም በረከት እንደማገኘ በእርግጠኝነት ተረዳሁ ፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ በትክከለኛው የክርስትና መስመር ጎዝ አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡

 የመጀመሪያው እርምጃዬ የእግዚአበሔርን ቃል በሚገባ መማር የተማሩትንም በተግባር ለማዋል መጣር ነበር፡፡ ቀጥሎ የንሥ አባት መያዝ፣ በንስ ከእግዚአብሔር ጋር ለመታቅ በጾም እና ጸሎት መትጋት ሆነ፡፡ ቀደም ብሎ በነበረው ሕይወቴ የኃላፊውን ዓለም ሀብት እና ንብረት ለመሰብሰብ የነበረኝ ጉጉት ሁሉ ቀረ፡፡ ዓለምን ናቁት መንገዴም አስተሳሰቤም ሁሉ በመንፈሳዊ ሆነ፡፡ አድራሻዬ ተለወጠ ቤተክርስቲያን መሄድ መጸለይ ማስቀደስ ትምህርት መማር መልካም ሥነ-ምግባርን ለመተግበር መጣጣር ለድሆች እና ለችግረኞች ማዘን፡፡

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያዘው ከንግድ ሥራዬ ከማገኘው ገቢ ላይ አራቱን በዕለቱ በመቀነስ ለብቻው በማስቀመጥ አጠራቅሜ ለቤተ ክርስቲያን መስጠት ጀመርኩኝ፡፡ ትኩረቴ ሁሉ መንፈሳዊ ነገር ላይ ቢሆንም ለረጅም ዘመን የገነባሁት የሥራ ባሕል ሥላለኝ ተግቼ ሥራዬን እሠራለሁ፡፡ ቀስ በቀስ የሥራዬ በረከት እጅግ ብዙ ሆነ፡፡ ለብዙ ዘመናት በሥራዬ ላይ የነበረው እንቅፋት በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት በእግዚአብሔር ቸርነት ተወገደልኝ፡፡

የእለት እንጀራ ለማግኘት እንዳልተቸገርኩኝ አሁን ግን የእግዚአብሔር በረከት ኑሮዮን መላ ተትረፈረፈ፡፡ በንግድ ሥራዬ የማገኘው ገቢ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ከማገኘው ገቢ  አሥራት ማውጣት ጀመርኩኝ፡፡ ገቢዬ እያደገ እኔም የማወጣው አሥራት ጨመረ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ቢሆንም አሥቴን አጠራቅሜ ሂሳብን ሠርቼ ለቤተ ክርስቲያን እሰጣለሁ፡፡ የድርጅቴ ሂሳብ ሠራተኞች በየዕለቱ ሂሳብ አንድ አሥረኛው ለይተው ከሌላ ገንዘብ ጋር ሳይቀላቅሉ በጥንቃቄ ያስቀምጣሉ፡፡ ይህ ሲሆን እነሆ ዘንድሮ ሰባተኛ ዓመት ሞላው፡፡

ገቢዬ እያደገ አሥራቱም እየጨመረ በጥቷል፡፡ የተጠራቀመውን ገንዘብ ከንግሥ በዓላቱ ጋር በማስታከክ ለህዳር ሚካኤል በዓል ሰሞን እና ለሰኔ ሚካኤል በዓል ግድሞ ወደ ቤተክርስቲያኑ አስተዳደር በመሄድ ደረሰኝ እያስቆረጥኩ እሰጣለሁ፡፡ በዚያን ሰሞን ብዙ መንፈሳዊ በረከት አገኛለሁ መንፈሳዊ ግዴታዩንም በመወጣቴ እግዚአብሔር እንደተደሰተ በልዩ ልዩ መንገድ አውቃለሁ ፡፡ የተለየ መንፈሳዊ ደስታ ይሰማኛል፡፡ በንግስ በዓሉ ዕለትም ነዳያንን ጦም አዳሪዎችን፣ ጸበል ጸዲቅ በማዘጋጀት ቡሉ ጠጡ በማለት መንፈሳዊ ግዴታዬን እወጣለሁ ፡፡

  ህዳር ሚካኤል በዓል ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀረው የግል ሥራዬን ትቼ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ቅድመ ዝግጅት ላይ ነበርኩ፡፡ በየዓመቱ የተለመደውን የአሥራት ገንዘቤን ሂሳብ ለማድረግ ከሂሳብ ባለሙያዎቼ ጋር ቡሰባ ተቀምጨ የአደራ ገንዘቡ የሆነውን አሥራቴን ቤተክርስቲያን ወስጄ ገቢ እስካደርግ በጣም ተቻኮልኩኝ መክንያቱም ደብራችን ለጀመረው የቤተክርስቲያን እድሳት ገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ሂሳቡ ሲሠራ ገንዘቡ በጣም ብዙ ሆነ፡፡ በሁለት ኩርቱ ፌስታል ሙሉ ገንዘቡን ቋጥሬ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመሄድ የለዱኩትን ተግባር በመፈጸም መንፈሳዊ በረከት እና ደስታ ለማግኘት ተዘጋጀሁ፡

 በሥራ ቦታ ካለወትሮው ባለጉዳዩች በዙብኝ፤ ከውጭ ሀገር ለሥራ ጉዳይ ስልክ ተደውሎ ረጅም ሰዓት አወራሁ፡፡ የእጅ ስልኬ ረጅም ሰዓት በመያዜ ባለቤቴ ስትደውል ስላላገኘችኝ ተከፋች፤ መልሼ ብደውልላትም ስልኩን አታነሳውም፡፡ ወደ ቤት መሄድ አለብኘ ቡዬ ተጣድፌ መኪናዬ ውስጥ ብገባ የመኪናዬ ሞተር እንቢ ብሎ ድርቅ አለ፡፡ ከሰዓታት በኋ በግፊ መኪናዬ ሲንቀሳቀስ ቅድሚያ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ ይገባኛ ብዬ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሄድኩ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሜ ጸሎቴን ስጨርስ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ህፈት ቤት በመሄድ ፈስታል የሞላውን የአስራት ገንዘብ ለአዲሷ ገንዘብ ያዥ ሳላስቆጥር ስልክ እያወራሁ ተቻኩዬ ከቤተክርስቲያን ወጣሁ፡፡

 ወዲውኑ የሰውነት አካሌን ሁሉ የሚቆረጣጥም ልቤን ፍርሃት ፍርሐት የሚል ስሜት ይሰማኝ ጀመር፡፡ ጉንፋን ወይም ብርድ ሆን ይችላል እቤት ሄጄ አረፍ ብዬ ሌሊት ቤተክርስቲያን እመጣለሁ በዬ አሰብኩኝ፡፡ ነገርግን ሕመሙ እየበረታብኝ ልቤን እየጨነቀኝ ሲመጣ ለምን ይሆን ? ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩኝ ፡፡ ላለፉት መታት ሳደርገው ከነበረው መንፈሳዊ ተግባር ያጎደልኩት ነገር የለም እንዲያው የዘንድሮው ከሌላ ጊዜ የተሻለ ነበረ፡፡

እቤት ገብቼ ትንሽ ስላመመኝ ልተኛ ብዩ ወደ መኝታ ክፍል ገባሁ፡፡ የመኝታ ሰዓቴ በቅዠት እና በጭንቀት አለፈ፡፡ አሥራ አንድ ሰዓት ሲሆን በግድ ሰውነቴን ጎትቼ ወደ ቤተ ክርስቲን ሄዱኩኝ፡፡ ጸሎተ ኪዳን አደረስኩ ቅዳሴም አስቀደስኩ፡፡ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ ዑደት ሲያደርግ እንደሌላው ጊዜ በእልልታ መዘመር አቃተኝ ሰውነቴ መቆም አቅቶት ራደ፡፡ ከዚህ በፊት በነበረኝ ተሞክሮ የአስራ ገንዘብ በሆነ መንገድ የጎደለ ወይም የዘገየ ከሆነ ሥራዬ ኑሮዬ ሁሉ መበታወክ ምልክት ይሰጠኝ ነበር፡፡ ዛሬም የሆነ የተፈጠረ ሥህተት ቢኖር ነው እንጂ በጤናዬ እንዳልሆነ ጠረጠርኩኝ፡፡ የዚህን ጊዜ እግዚአብሔርን ያስቀየምኩበት መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን ያስከፋሁበት ተግባር መኖር አምኜ ተቀበልኩኝ፡፡

 የአሥራት ገንዘቤን አጠራቅሜ በዓመት ሁለቴ በሰኔ ሚካኤል እና በህዳር ሚክኤል የንግስ በዓል ዕለት የመስጠት ልምድ አለኝ፡፡ ትዝ ሲለኝ ቢሮ ገንዘብ ማስቀመጫ ካዝና ውስጥ ስለነበር በሆነ መንገድ ከታሰበው ሂሳብ ላይ ቀንሰውለት ይሆናል ብዩ ገመትኩኝ፡፡ ወዲውኑ የእጅ ሥኬን አውጥቼ ወደ ጸሐፊዬ ደወልኩኝ፡፡ የመዝሙር እና የእልልታ ድምፅ አሰምታኝ ስልኩን ዘጋችው፡፡  ጭንቅ እንደያዘኝ ታቦቱ ዑደት አድረጎ ሲቆም ወደ ቤቴ አቀናው፡፡ እቤት ሄድ ማንም ሰው የለም የቤተሰቡ አባላት በሙሉ በዓል ለማክበር ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሄደዋል፡፡ ሶፋ ወንበር ላይ ጋደም እንዳልኩ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡    

ከእንቅልፌ የነቃሁት ቡና ፈልቷል ጸበል ጸሲቅ ቅመስ ብለው ሲቀቅሱኝ ነው፡፡ ወዲያው “ገብረ ሚካኤል” የሚል ድምፅ ሰማሁ የንስሐ አባቴ ናቸው፡፡ “በል ንቃ እንጂ ምነው? አመመህ እን ? አሉ” ተነስ በል ያዝ “እንካ በረከቱን ውሰድ ” ብለው የተቆራረሰ ዳቦ ያለበት ሳህን የያዘ እጃቸውን ዘረጉልኝ፡፡ ዳቦውን ለማንሳት ተንገዳግጄ ቆምኩኝ፡፡ የእንቅልፍ ድብርት እንዲለቀኝ መታጠቢያ ቤት ገብቼ ታጠብኩኝ፡፡ አሁን በመጠኑ ነቃሁ፡፡

 የንስሐ አባቴን በቅጡ ሰላምታ እኳን ሳልሰጣቸው “ዛሬ የሆነ ጥፋት ያጠፋሁ ይመስለኝል ለወትሮው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በማከብርበት ወቅት ይሰማኝ የነበረው መንፈሳዊ ደስታ ሁሉ ርቆኝ በዓሉን በህመም አከበረኩት” አልኳቸው፡፡ የንስሐ አባቴም “አታስለምድ አትከልክል” ይላሉ አባቶች “ካስለመድከው መንፈሳዊ ተግባር ያስቀረህው አለ እንዴ?” አሉኝ፡፡ አረ በፍጹም ጸበል ጸዲቁም ከተለመደው የበለጠ ሆኗል አስራቴንም ትናንትና ከፍያለሁ እንዲያውም ቤተ ክርስቲያኑ ሊያሰራው ላቀደው መጠለያ የተወሰነ ወጪ ይሸፍናል ብዬ እያሰብኩኝ ነበረ አልኩአቸው፡፡ በመሀል አቋረጡኝ እና “ለመሆኑ ስንት ብር ነው?” አሉ “ሦስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ብር ነዋ ” አልኩ፡፡

እግዚአብሔር ይመስገን በርትተህልኝል ሥራህ ሁሉ ተባርኮልሀል አሉ፡፡ ለመሆኑ ደረሰኝ አስቆረጥክ? ሲሊ ጠየቁኝ፡፡ እንዴታ አባ ለአዲሷ ገንዘብ ያዥ ወዲያው ነው ያስቆጠርኩት አልኮቸው፡፡ እስቲ የታለ አሉ ከሱሪዬ ኪስ ውስጥ ደረሰኝ አውጥቼ ሰጠዋቸው፡፡ ደረሰኙን ገና ሲመለከቱት በድንጋጤ እንዴ እንዴ ሦስትመቶ ሺህ ሰማንያ አምስት ሺህ አይደለ እንዴ ከፈልኩ የምትለኝ ደረሰኙን አይተህዋል ልጄ በቁጥርም በፊደልም የተጻፈው ሰማንያ አምስት ሺህ ነው እንዴ ስሙም እኳ ገብረሚካኤል ሳይሆን ኃይለሚካኤል ተብሎ ነው የተጻፈውብለው መስቀላችው ከፍ አድርገው አማተቡ፡፡

በህመሜ ላይ ይህ አስደንጋጭ ዜና ጭው የሚል ስሜት ተሰማኝ መረጋጋት አቃተኝ በድንጋጤ ባለሁበት ፈፍዤ ቀረሁ፡፡ ምንው ልጄ ደረሰኙን አይተህ አትቀበልም ነበር አሉ? በመገረም፡፡ አይ “አባ በጣም ቸኩዬ ስለነበር ብሩንም ሳላስቆጥር ነው በዛላይ ሰዓቱ ሲመሽ የባንክ ገልግሎት ዝግ በመሆኑ በቀጥታ ወደ ቤተክርስቲያን ይዥ መጣሁ” አልኳቸው፡፡ አይ ልጄ “ጊዜው እኳ ከባድ ነው ቅዱስ ሚካኤል ቤቱን እየጠበቀ ነው እንጂ ቡዙ ቀማኛ፣ ወንበዴ አለ ” ብለው ቁና ተነፈሱ፡፡ ኮስተር ብለው በል ልጅ የሆነ ነገር የተሠራ ኃጢአት አለ ለማንኛውም ቤተ ክርስቲያን ሄደን እናጣራብለው ተያይዘን ተጎዝን፡፡

አሁን ውስጤን ይሰማኝ የነበረው ድካም ፍርሀት በሙሉ ከእኔ እርቋል ተሳስሮ የነበረው ሰውነቴ ተፍታቷል፡፡ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተጠጋን ቁጥር ዛሬ ከእኔ እርቆ ላለፉት ስድስት ዓመታት ግን አብሮኝ የነበረ መንፈሳዊ ሀሴት ይሰማኝ ጀመር፡፡ ወደ ቤተክርስቲያኑ አስተዳደር ቢሮ ከንሥሐ አባቴ ጋር ገባን፡፡ ከቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ጋር ቀረቤታ ነበረን አንዳንዴም ለቤተክርስቲያኑ በአስቸኳይ የሚያስፈልግ ነገር ሲኖር ደውለው ያዙኛል፡፡ ቡራኬ ተቀብለን ተቀመጥን የሆነውንም ነገር ሁሉ ነገር ናቸው፡፡ በጥሞና አዳመጡኝ እና ደረሰኙን ትክ ብለው ተመለከቱት፡፡ ደግመው ደጋግመው አዩት ይሄነገር ሞዴል ሰላሳ ነው እንዴ አሉ? ምነው ቁጥሩ ፈዘዘብኝ ብለው ስልኩን አንስተው የቁጥጥር ክፍል ባለሙያውን ጠሩት፡፡ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ከመቀመጫቸው ተነሱ አንገታቸው ላይ የደረቡትን ጥቁር ልብስ አውልቀው ጠረጴዛ ላይ አስቀመጡ የቅዱስ ሚካኤል ያለህ ምንዐይነት ጉድነው በማለት አዘኑ ታቸው ቀላ ተኮሰታተረ፡፡

 የቤተክርስቲያኑ የቁጥጥር ባለሙያ መጣና በፊታቸው ቆመ “ከሂሳብ ሹሙ ጋር ሆናችሁ ከትናንት ጀምሮ በደረሰኝ የገባውን ገቢ አሁኑኑ አሳውቁኝ ደረሰኛችሁን ይዛችሁ ኑና እዚህ እኔ ፉት ሥሩ” አሉ፡፡ ቁጥሩ አባታችን ግማሹ ደረሰኝ ለት ገንዘብ ሰበሰሳቢዋ ጋር ነውለ፡፡ አሰተዳዳሪውም ቆጣ ብለው “እሷንም ፈልጋችሁ አንድ ላይ ኑ ”ብለው ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡ እነርሱ ወጣ እንዳሉ ስልካቸውን አነሱና የበቃ ኃላፊውን ጠሩት ወዲያውኑ መጣ፡፡ የጥበቃ ኃላፊውን መስቀል አሳልመውት ወደ ጆሮው ጠጋ ብለው የሆነ ነገር በሹክሹታ ነገሩት እሺ ብሎ ወጣ፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ “ለመሆኑ ገንዘብን የተቀበሎት ማነው”? ብለው ጠየቁኝ፤ አባታችን አዲ ሴቷ ገንዘብ ያዠ ናት አልኩኝ ፡፡ በምን ሰዓት ነው አሉ ? ወደ ማታ ላይ አሉና መለስኩኝ ፡፡ ጥያቄያቸውን ቀጠሉ ገንዘቡን ስታስረክብ አብሮዎት ማን ነበር? ብለው ጠየቁኝ፡፡ አረማንም አልነበረም ብቻዬን ነበረኩኝ አልኩኝ፡፡ ቆይ እሺ ደረሰኙ በሌላ ሰው ስም ሲፃፍ ለምን ዝም ብለው ተቀበሉ? አሉኝ፡፡ ወዲያው አስተውዬ አላየሁትም አልኳቸው ፡፡ ሌላ ጥያቄ ሳይጠይቁኝ ቁጥጥሩ እና ሂሳብ ሹሙ መጡ፡፡

ሂሳብ ሹሙ “እስከ አሁኑ ሰዓት በደረሰኝ የገባዉ ገንዘብ ከመቶ ሃያ ሺህ ብር በላይ ነው” አለ፡፡ አስተዳዳሪው ተቆጥተው እርሱን አይደለም የጠየኩህ ከትናንት ጀምሮ ተቆረጠውን ደረሰኝ፣የገባውን የገንዘብ መጠን፣ ያስገባውን ሰው ስም ፣የደረሰኝ ቁጥር በቅደም ተከተል በነጭ ወረቀት ላይ ጻፉልኝ አሉ፡፡

 በሩ ተንኳኳ የቤተከርስቲያኑ ጸሐፊ እና የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር ነበር የመጡት፡፡ አስተዳዳሪው መጣችሁ ለአስቸኳይ ጉዳይ ፈልጋችሁ ነበር አዳራሽ ሆነን እናውራ ብለው ተነስተው ወጡ፡፡

ሂሳብ ሹሙ እና ቁጥጥሩ መረበሽ ይታይባቸዋል፡፡ ሂሳብ ሹሙ በጎሪጥ ተመለከተኝ፡፡ እኔም ፍጥጥ ብዬ አየሁት እና “ለመሆኑ የእለት ገንዘብ የምትሰበስበዋ ወዴት ሄደች አልኩት” ቆጣ በዬ፡፡ እርሱም በተራው “እኔ እንጃ አላውቅም” አለ በአጭሩ፡፡ የንስሐ አባቴ ብዙ የሚያውቁት ነገር ለ ይመስለኝል መስቀላቸውን በእጃቸው እየመቱ ዝም ብለው ቁጭ ብለዋል፡፡ ሂሳብ ሹሙ ከደረሰኙ ላይ የገለበጠውን የገቢ መጠን በዝርዝር አስቀምጦል አንደኛ ሁለተኛ እያለ እስከ ሃያ መድረሱን ለቁጥጥሩ ይነግረዋል፡፡

በሩ ተከፈተ የቤተ ክርስቲያኑ አሥተዳዳሪ የሰበካ ጉባኤው አባላት ጸሐፊው ሆነው መጡ አስተዳዳሪው የተመዘገበውን የደረሰኝ ውጤት ለማየት ጎጉተዋል፡፡ ገና ሳይቀመጡ የመዘገብከው የታለ ብለው ተቀብለው ማንበብ ጀመሩ አንደኛ የገቢ መጠን አምስት ሺህ ብር ሁለተኛ ሦስተኛ እያሉ እስከ ሃያ ድረስ አነበቡ፡፡ ሦስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ብር የሚል ገንዘብ ደረሰኙ ላይ አልተመዘገበም፡፡  ይህን ስሰማ ደነገጥኩኝ እና ላብ አሰመጠኝ፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ከጠረጴዛቸው ስር ያስቀመጡትን ደረሰኝ ብድግ አድርገው እያሳዩ ይህን ደረሰኝ ማነው የቆረጠው ቁጥሩ 0012 ይላል ብሩስ የት ደረሰ አሉ፡፡ የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር በተቃጠለ ስሜት ቁጣ ቁጣ እያላቸው “የምትጠቀሙበት የደረሰኝ ቁጥር ከስንት ነው የሚጀምረው” ቡለው ቁጥጥር ክፍሉን ጠየቁት፡፡ እርሱም መልሶ “አሁን እየተጠቀምንበት ያለው ከ 0705 ጀምሮ ነው” ብሎ መለሰ፡፡

አስተዳዳሪው “ከያዛችሁት ዝርዝር ውስጥ ስምንት መቶ ሃምሳ ብር የሚል የሰማው መሰለኝ እርገጠኛ ለመሆን እቲ ዝርዝሩን እዩት” አሉ፡፡ ሂሳብ ሹሙ ወረቀቱን ተመልክቶ አዎ አለ፡፡ የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበሩም እሺ በማን ስም ነው የተቆረጠው ?አሉት ሂሳብ ሹም መለሰ በገብረ ሚካኤል ነው አለ ፡፡ በሆነው ነገር ሁሉም ተገርመው አዘኑ፡፡

የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪው በቁጣ እዚህ ቤት በሁለት ደረሰኝ በመጠቀም ወንጀል እየተሰራ ነው፡፡ የሚካኤልን መገበሪያ ሰርቆ የበላ ሳይለፈልፍ አይቀርም እንዲሉ አበው ቅዱስ ሚካኤል ደግሞ በዕለተ ቀኑ በዓመተ ክብሩ ሌባዉን እያጋለጠ ተአምራቱን አየራ ነው፡፡  የእግዚአብሔርን ገንዘብ የሚሰርቅ የይሁዳ ቢጤ የምዕመናንን ገንዘብ የሚዘርፍ ሌባ ማነውበማለት በቁጣ ተናገሩ፡፡ አስተዳዳሪው ለዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዋን ስልክ ደወላችሁ ብለው ጠየቁ ፡፡ ተደውሎላት ቶሎ እመጣለሁ ብላለች አለ ጸሐፊው፡፡

በሩ ተንኳኳ የጥበቃ ኃላፊው ነው የተጠሩት መጥተዋል አለ ለአስተዳዳሪ መልካም መጣሁ አንዴ ጠብቁኝ በላቸው አሉት፡፡ የጥበቃ ኃላፊ በሩን ሊዘጋ ሲል የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዋ መጣች መስቀል ተሳልማ ቁጭ አለች፡፡

የሰበካ ጉባኤው ሊቀመንበር እኔ ልቅደም በሚል ፈጠን ብለው “እንዴት ዋልሽ  ለአንድ ጉዳይ ፈልገንሽ ነበር ” አሏት፡፡ ገንዘብ ተቀባይዋ ሴት ኳስተር ብላ “ ለምን ነበር” አ፡፡  ሊቀመንበሩ ቀጥለው እኝህ ወንድ ማችን እዚህ ደብር ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያናች በገንዘባቸው በጉልበታቸው አገልጋይ ናቸው፡፡ ትናንት አንቺ ዘንድ መጥተው ገንዘብ ሲያስገቡ በስም ተሳሳተና ኃይለሚካኤል ተብሎ ደረሰኝ ተቆረጠላቸው በዚህ ቅር ተሰኝተው ነው፡፡ ስለዚህ ተስተካክሎ ደረሰኝን እንዲቆረጥላቸው ደረሰኙን አምጨውና እዚሁ ሁላችንም ባለንበት ተሰርዞ ሌላ ደረሰኝ ይቆረጥላቸው አሉ፡፡ በሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር የንግግር ብልሀት ሁላችንም ተገረምን አዋ ብለን ደገፍ ናቸው፡፡

 እኔም ቀጠል አድርጌ በእውነቱ ከሆነ እኔም የክርስትና ስሜ ተቀይሮ ደረሰኝ በመረጡ በጣም አኛለሁ አልኩ፡፡ የዕለት ገንዘብ ሰብሳቢዋ አንደበቷ ተሳስሮ ግራ በመጋባት ስሜት ተቁነጠነጠች እና “የካዝና ቁልፍ አልያዝኩም ” ብላ መልስ ሰጠች፡፡ የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር “እንዴ ደረሰኙም እንደ ብሩ በካዝና ነው እንዴ የሚቀመጠው” ሲሏት “የኮመዲኖ ቁልፍ ” ማለቴ ነው አለች፡፡ ኮሞዲኖው ተሰብሮም ቢሆን ደረሰኙ መውጣት ስላለበት ከጥበቃ ኃላፊው ጋር አብረሽ ሂጂ ተባለች፡፡

  ከቢሮው ስትወጣ ሁለት ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶች ጠበ፡፡ ፖሊሶቹን ስታይ ለምንድ ነው የመጡት ስትል በፍርሀት ሆና ጠየቀች፡፡ ፖሊሶቹም የወንጀል ድርጊት መፈጸሙን በመጠርጠሩ ነው ብለው ወደ ቢሮዋ አብረው ሄዱ፡፡ ቢሮዋ ሲከፈት የደረሰኝ ጥራዝ እና ጥሬ ገንዘብ ሃምሳ ሺህ ብር ተገኘ፡፡ ከፖሊሶቹ ጋር ተመልሳ ወደ ስብሰባው ቦታ መጣች፡፡ የሰበኮ ጉባኤው ምክትል ሊቀመንበር ጥያቄአቸውን ቀጠሉ ከገብረ ሚካኤል ገንዘብ ተቀብለሻል? አሉአት አዎ ብላ መለሰች፡፡ ምን ያህል? አሉዋት ሰማንያ አምስት ሺህ ብር ብቻ ለእርሱም ደረኝ ተቆርጦላቸዋል አለች፡፡ ገንዘቡ የት አለ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ገቢ ተደርጎል ለማን ሰጠሽ “ለሂሳብ ሹም” አለች፡፡ የቆረጥሽው ደረሰኝ የቤተክርስቲያኑን ነው ማለት ሞዴል ሰላሣን ነው ተባለች መልስ ሳትሰጥ አቀረቀረች ፡፡

የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ እስቲ ገብረሚካኤል ስንት ብር ነው ይዘህ የመጣህው ዝም አትበል ተናገር እንጂ አሉኝ፡፡ የሆነውን ነገር ማመን አቅቶኝ ግራ ገባኝ እኔ የብዙ ጊዜ የተጠራቀመ ስለነበር ብሮዬ ከሂሳብ ሠራተኛዬ ጋር ሆኜ ገቢዬን አስልቼ አንድ አስረኛውን ሥስት መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ብር በሁለት ፌስታል ነው እንደተለመደው ያመጣሁት እንዲያውም ቸኩያለሁ አልቆጠርኩትም ብዮ ተናግራለሁ በወቅቱ ስልክ እያወራሁ ደረሰኙን ተቀብዬ ኪሴ ውስጥ ከትቼ ብቻ ሳላየው ሄድኩኝ ብዬ በከፍተኛ ቁጣ መናገር ጀመርኩኝ፡፡

የሰባካ ጉባኤ ሊቀመንበሩ በመካከላችን ፖሊሶችም ስላሉ የዕለት ገንዘብ ያዥ እና ሂሳብ ሹም ለፖሊስ ቃላቸውን ይስጡ፡፡ ፖሊሶች የሚፈልጉትን ማስረጃ በሙሉ ወስደው ምርመራ ያድርጉ፡፡ ለቤተክርስቲያን ለሚመለከታቸው አካላት ቃለጉባኤ ተፈራርመን ሁኔታውን በደብዳቤ እናሳውቅ አሉ፡፡ በዚህ ሀሳብ ሁሉም ተስማሙ፡፡ የእለት ገንዘብ ያዥዋ የነገሩን ቁርጥ መሆኑን ስታውቅ እያለቀሰች ተሳስቼ ነው የልጆች እናትነኝ እባካችሁ ኑሮን ለማሸነፍ ነው እያለች ተርበተበተች ማልቀስም ጀመረች ሁሉንም አላጠፋሁትም ግማሹ አለ የሂሳብ ሹሙ ነው ይህን ዘዴ የነገረኝ እያለች ቡዙ መለፍለፍ ጀመረች  ፖሊሶቹ አይዞሽ ቃልስን ብቻ ነው የምትሰጪው እያሉ ይዘዋት ሄዱ፡፡

በሆነው ነገር በጣም አዘንኩ ሌብነትን ወንጀልን ተጠይፌ አይሆንም በንፁህ እጄ ሠርቼ ማግኘት አለብኝ በማለት ያሳለፍኳቸው የድህነት ጊዜያት አስታወስኩ፡፡ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት በእግዚአብሔር ቸርነት የዚህን ዓለም ኑሮን ለማሸነፍ የማደርገው ፍልሚያ ትቼ ለሚበልጠው ዘላለማዊ ተስፋ የእግዚአብሔር መንግስት የምሮጥ ሆንኩኝ፡፡ የዚህ ዓለም ሀብት ከንቱ እንደሆ እግዚአብሔርን ከቀረብኩት ጊዜ ጀምሮ ተረድቻለሁ ፡፡ ገንዘብ ዘላለማዊ ሕይወት መዘጋጃ መሳሪያ መሆኑን ስለተረዳሁ ሳገኝ ለችግረኞች ስሰጥ አስራቴን ሳወጣ የቅዱሳን መታሰቢያ ሳከብር የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን ስረዳ የተቸገረን ስጠይቅበት የቀደመውን ያህል ብዙ ሳልደክም ሕገ እግዚአብሔርንም ሳልጥስ በቀላል ድካም ብዙ በረከት አገኘው፡፡ 

ኑሮን ለማሸነፍ በምሮጥበት ጊዜ የስኬት መንገድ በጠፋኝ ሰሞን ምክርን ይለግሱኝ የነበሩ ወዳጆቼን ሁሌም አስታውሳቸዋለሁ፡፡ ኑሮን አሸንፌ በብዙ መልኩ ውጤታማ የሆነ የበረከት ኑሮ ስኖር እኔም በተራዮ የስኬቴ መንገድ ከእግዚአብሔር ጋር መተዋወቅ እንደሆነ እንግራቸዋለሁ፡፡ ሥራ ቦታዬ በመጡ ቁጥር በየግድግዳው ላይ በፍሬም የለጠፍኮቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እያሳየሁ ማብራሪያ እሰጣለሁ፡፡ በተለይም አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግስት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል ማቴ 6፥33 የሚለው የወንጌል ቃል እንዲሁም አንተ የመረጥከው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልከው ምስጉን ነው ከቤትህ በረከት እንጠግባለን፡፡ የሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር 65፥4 በመጥቀስ እመሰክርላቸዋለሁ፡፡

 ዛሬ በቅዱስ ሚካኤል በዓል ከዋዜማው ጀምሮ በሆነው ተአምራት ይበልጥ ወደራሴ ተመለከትኩኝ ራሴን ወቀስኩበት ትምህርት አገኘሁበት፡፡ ኑሮን ለማሸነፍ ባደረኩት ትንንቅ እግዚአብሔርን ቀረብኩት አወቅኩት፡፡ ይበልጥ ስቀርበው የዚህ ዓለም ገንዘብ ኃላፊ ጠፊ መሆኑን ተረዳሁ፡፡ ብቸኛው የኑሮ ስኬት የተቃና ሕይወት መንገድ እግዚአብሔርን መቅረብ ማወቅ ሕጉን እና ትእዛዙን አክብሮ መስራት መሆኑን ተረዳሁ ሰዎች ይህን ባለመረዳት ከእግዚአብሔር በልዩ መንገድ በተለያየ ስፍራ ይሰርቃሉ በረከታቸውንም ያጣሉ፡፡   

በ ያዕቆብ ሰንደቁ

የካቲት 29 /2014

œ

ማክሰኞ 28 ኦገስት 2018

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

«ለጊዜው ብቻ ያምናሉ» ሉቃ.8፥13

በክረምት ወቅት ተነበው ስብከት ከሚሰበክባቸው የቅዱስ ወንጌል ምንባብ መካከል አንዱ የዘሪው ምሳሌ ተብሎ የሚጠራው የምንባብ ክፍል ነው፡፡ ይህን በምሳሌ የተነገረውን ትምህርት ሦስቱ ወንጌላውያን ማለትም ቅዱስ ማቴዎስ፣ ቅዱስ ማርቆስ፣ ቅዱስ ሉቃስ ጽፈውታል፡፡

የምሳሌያዊ ትምህርቱ ዋና መልዕክት አንድ ገበሬ በሚዘራበት ወቅት ዘሩ በተለያየ የማሳው ቦታ ላይ እንደሚወድቅ የወደቀበትም መሬት ሁኔታ ለዘሩ መብቀል መጠውለግ ብሎም ፍሬማ መሆን ምክንያት መሆኑ ማስረዳት ነው፡፡ ከዚህም ምንባባት መካከል ቅዱስ ሉቃስ ከጻፈው ምንባብ ወስጥ ገበሬው ከዘራው ዘር መካከል በዓለት ላይ እንደሌሎቹ ወንጌላውያን አባባል በጭንጫ መሬት ላይ የወደቀውን ዘር አበቃቀል ከዚያም ፍሬ ሳይሰጥ መድረቁን እንመለከታልን፡፡

ይህን በምሳሌ የተነገረው ቅዱሳን ሐዋርያት ትርጉሙን መረዳት ባለመቻላቸው ጌታቸውን መምህራቸውን ጠይቀውት ነበር፤ እርሱም ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን በዓለት ላይም የወደቀው ዘር ሥር ሳይሰድ ለጊዜው ብቻ ማደጉ እርጥበት ስላልነበረው ፥ፀሐይ በወጣ ጊዜ ግን መጠውለጉን፥ በፍጥነትም መድረቁን ነግሯቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሚዘራበት ልቦናቸው ዓለት ጭንጫ መሬት የሆነቦቸው ሰዎች ቃሉን ሰምተው ወዲያውኑ በደስታ የሚቀበሉ ለጊዜው ብቻ የሚያምኑ በቃሉ ምክንያትም መከራ ወይም ስደት በሆነ ጊዜ ወዲያው የሚሰናከሉ በፈተና ጊዜ የሚክዱ ሥር የሌላቸው ናቸው። ማቴ.13 ፥1 ማር 4፥1 ሉቃ.8 ፥13

«…እናንተ ሆይ፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይጋልባሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?» በማለት ነቢዩ አሞጽ የጭንጫ መሬት ለፈረስ ግልቢያም ለእርሻም እንደማይሆን ይናገራል፡፡ አሞጽ 612-13  የመሬቱም ጠባይ ለፍሬው ዕድገት የሚረዳውን ውሃ የማይቋጥር ፣ሥሩ ቆንጥጦ የሚይዝበት አፈር የሌለው፤ በእርሱ ላይ የበቀለውም ለጊዜውም ብቻ በቅሎ ነገርግን አቅም ስሌለው ፀሐይ መቋቋም ባለመቻሉ የሚደርቅ ነው፡፡ በጪንጫ መሬት ላይ የተዘራ ዘር ለጊዜው በመብቀሉ እና ቅጠል በማሳየቱ ብቻ በስተመጨረሻ ግን አብቦ አያፈራም፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወትም የእግዚአብሔርን ቃል ለአንድ ሰሞን ይሁን ለረጅም ዘመን የሰማ ብቻ መንፈሳዊ ፍሬ አያፈራም፡፡ በምግባር በሃይማኖት በመጽናት የፀሐዩን ሀሩር ለመቋቋም በጥልቅ መሠረት ላይ መተከል አለበት አንጂ፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም « ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ ቃሌንም ሰምቶ የሚያደርገው፥ ማንን እንዲመስል አሳያችኋለሁ። ቤት ሲሠራ አጥልቆ የቆፈረ በዓለት ላይም የመሠረተ ሰውን ይመስላል፤ ጐርፍም በመጣ ጊዜ ወንዙ ያን ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ ሊያናውጠው አልቻለም። ሰምቶ የማያደርገው ግን ያለ መሠረት በምድር ላይ ቤቱን የሠራ ሰውን ይመስላል፤ ወንዙም ገፋው ወዲያውም ወደቀ የዚያ ቤት አወዳደቅም ታላቅ ሆነ።» ሉቃ.6 ፥ 47-49 ማቴ 7፥25  

ጐርፍም በመጣ ጊዜ ወንዙ ያን ቤት ገፋው፥ በዓለት ላይም ስለ ተመሠረተ ሊያናውጠው አልቻለም የተባለው በትክክለኛ መንፈሳዊ መሠረት ላይ የተመሰረተ ክርስቲያናዊ ሕይወትን ነው፡፡ መንፈሳዊ ሕይወትም በምግባር በሃይማኖት ጥልቅ መሠረት ላይ የተመሠረተ ከሆነ ሊያጠፋው የሚመጣበተን ፈተና በሙሉ የመቋቋም ኃይል አለው፡፡ በጭንጫ መሬት ላይ እንደበቀለችው ቅጠል ለጊዜው አምሮ ተውቦ የፀሐዩን ንዳድ ትኩሳት ማለትም ፈተናንን ማለፍ ሳይችል ቀርቶ አይወድቅም፡፡ ሐዋርያው ጳዉሎስም በመልእክቱ “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” ኤፌሶን 220  ያለው መልዕክት ይህን ይበልጥ ያስረዳልናል፡፡

የነቢያት መሠረት እና የሐዋርያት መሠረት የእውነት እና የጽድቅ ነበር፡፡ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ብዙ መከራን በአሕዛብ ፊት ከምስክርነታቸው የተነሳ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት እና ነቢያት በመልካም መሬት ላይ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወት መሥርተው ነበር፡፡ በዘመኑ የገነነው ንጉሥ ነቢያትን እንደሰም ሳያቀልጣቸው፣ ቅዱሳን ሐዋርያትን የሮም ፀሐይ ሳያጠወልጋቸው፤ ቤታቸውን ሊያፈርስ የመጣው ጎርፍ ከሃይማኖት ሳያናውጣቸው ቀርቷል፤ አንገታቸው እኪቀላ ድረስ፣ ቆዳቸው እኪገፈፍ ሰማዕትነትን ተቀብለው በሃይማኖት ቆሙ፡፡ ደስ እያላቸውም በብዙ ድካም እና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ልንገባ ይገባናል በማለት በምግባር ፀኑ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ “በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ” ኤፌሶን 316-17  እንዳለ የቤታቸው የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማድረግ በልባቸው አኖሩት ሥር መሠረታቸውም ለዓለም ሁሉ ቤዛ ለመሆን በቀራንዮ አደባባይ በተሰቀለው በመድኃኒታችን ፍቅር ሆነ ፡፡

በጪንጫ መሬት ላይ የተዘራ ዘር ለጊዜው በቅሎ ነበር ሥሩን ወደ ወንዝ ዳር ሳይሰድ በመቅረቱ በድርቅ ዘመን ፀሐዩ ሲበረታ ፍሬውን አቋረጠ ደረቀ፡፡ ነቢዩ ኤርምያስንም ይህን በማስመልከት የጻፋ ምንኛ ድንቅ ይሆን እንዲህም ይለናል “በእግዚአብሔር የታመነ እምነቱም እግዚአብሔር የሆነ ሰው ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፥ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ሙቀትም ሲመጣ እንደማይፈራ ቅጠሉም እንደሚለመልም፥ በድርቅ ዓመትም እንደማይሠጋ ፍሬውንም እንደማያቋርጥ ዛፍ ይሆናል።”  ኤርም 178

ፍሬው የማያቋርጠው ዛፍ ዕምነቱ በእግዚአብሔር ላይ ነው፤የሚመጣውንም ፈተና እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ድል ያደርጋል፡፡ ሥሮቹን ዘርግቶ ሕይወት የሆነውን ውኃ እንደሚጠጣ ተክል ከሕይወት ውኃ ከእግዚአብሔር ቃል ይጠጣል እና በድርቅ ዓመት በክፉ ዘመን አይሰጋም አይደናገጥም ለጌዜው ሳይሆን እስከመጨረሻው ያምናል፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት ሳያቋርጡ የምግባር የሃይማኖት ፍሬ መስጠት የሚቻለው በውኃ ዳር በተመሰለች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተተክሎ ሥርን ዘረግቶ ከትምህርቷ ሲቀዱ ብቻ ነው፡፡ የነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት መዝሙር ይህን ያስታውሰናል “ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።” መዝሙረ ዳዊት 1

በጪንጫ መሬት ላይ የተዘራ ዘር ለጊዜው በጣም በፍጥነት ነበር የበቀለው፡፡ ይህም ገበሬው የድካሙን ፍሬ እንዲያይ በቅጠሉ ማማር እና መስፋትት እዲደሰት ለፍሬውም ተስፋ አንዲያደርግ አድረጎት ነበር፡፡ ይህም ፈጥና ጥላ ሆና ከአፍታ ቆይታ በኋላ የረገፈችውን የነቢዩን ዮናስ የቅል ዛፍ ታስታውሰናለች፡፡ “ዮናስም ከከተማይቱ ወጣ፥ ከከተማይቱም በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ ከተማይቱንም የሚያገኛትን እስኪያይ ድረስ በዚያ ለራሱ ዳስ ሠርቶ ከጥላው በታች ተቀመጠ። እግዚአብሔር አምላክም ቅል አዘጋጀ፥ ከጭንቀቱም ታድነው ዘንድ በራሱ ላይ ጥላ እንድትሆን በዮናስ ላይ ከፍ ከፍ አደረጋት ዮናስም ስለ ቅሊቱ እጅግ ደስ አለው።በነጋው ግን ወገግ ባለ ጊዜ እግዚአብሔር ትልን አዘጋጀ፥ እርስዋም ቅሊቱን እስክትደርቅ ድረስ መታቻት። ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ ዮናስ እስኪዝል ድረስም ፀሐይ ራሱን መታው ለራሱም ሞትን ፈለገና። ከሕይወት ሞት ይሻለኛል አለ። እግዚአብሔርም ዮናስን፦ በውኑ ስለዚች ቅል ትቈጣ ዘንድ ይገባሃልን? አለው። እርሱም፦ እስከ ሞት ድረስ እቈጣ ዘንድ ይገባኛል አለ።እግዚአብሔርም፦ አንተ ትበቅል ዘንድ ላልደከምህባት ላላሳደግሃትም፥ በአንድ ሌሊት ለበቀለች፥ በአንድ ሌሊትም ለደረቀችው ቅል አዝነሃል።እኔስ ቀኛቸውንና ግራቸውን የማይለዩ ከመቶ ሀያ ሺህ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሶች ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አላዝንምን? አለው።” ትንቢተ ዮናስ 4፥3-11

በአንድ ለሌት የበቀለች በአንድ ለሌት የደረቀችው የቅል ቅጠል ነቢዩ ዩናስ ለረጅም ጊዜ ጥላ ትሆነኛል ብሎ ተስፋ አድረጎ ነበር፡፡ይልቁኑ ትበቅል ዘንድ ላልደከመባት እና ላላሳደጋት ቅል እንዲ ማዘኑ ያስገርማል፡፡ እግዚአብሔር ለተከላቸው እና ላበቀላቸው በሕይወት እንዲኖሩም ተስፋ ያደረገበቸው መቶ ሃያ ሺህ የነነዌ ሰዎች በፍጥነት ወደ ጥፋት መግባት ምንኛ ያሳዝን፡፡ በስተመጨረሻም ነቢዩ ዮናስ የሰዎቹ መጥፋት ገዶት በከተማዋ ተዘዋውሮ የአዋጅ ነጋሪ ሆኖ ጾም ጸሎትን ሰበካቸው፡፡ ግራና ቀኝ የማታውቀው ከተማ በነቢዩ ዮናስ አዋጅ ከመጣባት እሳት በንስሐ እና በዕንባ መለምለም ችላ ፍሬዋን አፍራች፡፡

ዛሬም በአንድ ለሌት መንፈሳዊያን በአንድ ለሌት ደግሞ ጭልጥ ያለ አረመኔ የሚሆኑ ሰዎቸን እግዚአብሔር ከሚመጣው ቁጣ ይድኑ ዘንድ ምን ያህል ያዝንላቸው ይሆን? ግራና ቀኙን የማያውቀው የእግዚአብሔር ተክል የሆነው ምዕመን በታላላቆቹ ከተሞች ተሰግስጎ ተቀምጧል፤ እንደ ነቢዩ ዮናስ ስለራሱ መጠለያ፣ ጥላ፣ ፈረጅያ ሳይጨነቅ በየገጠሩ በየስርጡ እየዞረ የንሥሐን ፍሬ ያፈሩ ዘንድ የአዋጅ ነጋሪ ቃል የሚነግራቸው ማን ይሆን? ራሱ ከሚያገኘው ድቃቂ ሳንቲም አስበልጦ በነፍሳቸው ስለሚጠፉ ምእመናን የሚጨነቅ አገልጋይ ማን ይሆን? እሳት የተቃጣበት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር በታላላቅ ከተሞች ያለ የማያፈራ ምዕመን ፉቱን ወደ ንሥሐ ይመልስ ዘንድ የማንቂያውን ደውን የሚያስጮህ ፍሬአማ ጽኑ አገልጋይ ለ ቤተ ክርስቲያን ይፈልጋታል፡፡

የፀሐይ ከትኵሳት ቅጠልን ሣርንም እንዲያጠወልግ፥ አበባውንም እንደሚያረግፍና፥ የመልኩም ውበት እንደሚያጠፋ ፤በጪንጫ መሬት ላይ የተዘራ ዘር ከበቀለ አና ቅጠል ካወጣ በኋላ ከሌሎች ተክሎች ተለይቶ ፀሐዩን መቋቋም ያቅተዋል፡፡ ፀሐይ ለሁሉም ሳታዳላ እንደምትወጣ ማንኛውም ክርስቲያናዊ ሕይወት ፀሐይ የተባለ ፈተና ያጋጥመዋል፡፡ ይህንንም በጽናት ተቋቁሞ ማሳለፍ ይጠበቅበታል፡፡ ሐዋርያው ያዕቆብም ሲመክር ፈተና ለክርስቲያኖች የማይቀር ነውና በመጣባችሁ ጊዜ ጠውልጋችሁ አትዘኑ በደስታ ተቀብላችሁ ተቋቁማችሁት እለፉት ይለናል “ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።ማንም ሲፈተን። በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል።ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።” ያዕቆ 1፥1- 14፣ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 16-7

ክርስቲያናዊ ሕይወት እንደወርቅ በእሳት ተፈትኖ ማለፍ መሆኑ ያልተረዱ ሰዎች ይክዳሉ፡፡ ለዚህም ዋነኛ ምክንያታቸው ሥር ሰደው ያልታነጹ ሃይማኖታቸውን በሚገባ ያልተረዱ መሆናቸው ነው፡፡  ሐዋርያው ጳውሎስም ቆላስይስ ሰዎች የመከራቸው እንዲህ በማለት ነበር “ሥር ሰዳችሁ በእርሱ ታነጹ፥ እንደ ተማራችሁም በሃይማኖት ጽኑ፥ ምስጋናም ይብዛላችሁ። እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፥ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።” ብሎአል፡፡ ቆላ 2፥7፣ ሮሜ ሰዎች 11፥15-17 ሮሜ 15፥14

 ብዙ ተደክሞበት ሳለ ነገርግን መሠረቱን ጥልቅ ያላደረገ በሃይማኖት ያልታነጸ ምዕመን እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ ትምህርት ባለ በፍልስፍና በከንቱም ይታለላል እንደዚ ያሉትን ሰዎች ነቢዩ በግሩም ቃል እንዲህ በማለት ይገልጻቸዋል “ተክለሃቸዋል ሥር ሰድደዋል፤አድገዋል አፍርተውማል፤ በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፥ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።» ትንቢተ ኤርም 12፥1-2 ነቢዩ ኤርምያስ እንዳለው የማያቋርጥ ፍሬ የሌላቸው ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ሕይወት በጽኑ መሠረት የታነጸ ሳይሆን በአንደበታቸው ብቻ ቃሉን የሚናገሩ ቅንጣት ታክል እንኳን መልካም ሥራ የሌላቸው የአምልኮ መልክ ብቻ ያላቸው ናቸው፡፡ እነዚህን የመጨረሻው ዘመን ሰዎቸን ምን አይነት ጠባይ እንዳላቸው ቅዱስ ጳውሎስ ለደቀ መዝሙሩ ለጢሞቴዎስ በላከው መልእክቱ ላይ ይገልጸዋል “ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።”  2 ወደ ጢሞቴዎስ 3፥1-3

ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ሰዎች ችኩሎች ስሆኑ ለጊዜው ብቻ ያምናሉ መልካም የሆነውንም የማይወዱ ጨካኞችም በመሆናቸው አያመሰግኑም ቅድስናም የላቸውም፡፡ የእግዚአብሔርን ኃይል ስለሚክዱ በሃይማኖት በምግባር አይጸኑም፡፡ ሃይማኖተኝነት በጊዜ ገደብ የሚወሰን ሲያመቸን የምናጠብቀው ሌላ ጊዜ ደግሞ የምንተወው አይደለም ዋጋ መንግሥተ ሰማያት የሚሰጠው ጀምረን ባቋረጥነው ሳይሆን እስከመጨረሻው ህቅታ ድረስ በፈጸም ነው ፡፡ ይህን በማስመልከት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለዕብራውያን ሰዎች የጻፈው መልእክት ምንኛ አስተማሪ ነው «የመጀመሪያ እምነታችንን እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ፥ የክርስቶስ ተካፋዮች ሆነናልና፤» ዕብ.314 የክርስቶስ መንግስት ተካፋይ ለመሆን መጽናት ያሻል ቅዱስ ጳውሎስ ተማሪውን ጢሞቴዎስን በማስተማሩ ተግባሩ እንዲጸና ቃሉን ስበክ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 42  ብሎታል፡፡ ጊዚያዊ ክርስትና ጊዜያዊ ዕምነት የለም “እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።” ማቴ 1022

ናዝሬት ደብረ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን  የተሰበከ

ቅዳሜ 21 ሜይ 2016

ስብከት

አንድ ፍቅር አንድ ልብ

ሰዎች እግዚአብሔርን የሚያመልኩት የሚወዱት ባልተከፋፈለ በአንድ ልብ ነው፡፡ እስራኤላውያን የጸና እና የተረጋጋ ልብ ስላልነበራቸው ወላዋዮች በአምልኮተ እግዚአብሔር የማይጸኑ ነበሩ ፡፡ ይህን የተረዳው እግዚአብሔር በመሪያቸው በሙሴ አማካኝነት አምላካቸውን በአንደበታቸው ሳይሆን በአንድ ልብ፤ በአንድ ሀሳብ እንዲወዱ እና እንዲያመልኩት አዘዛቸው፡፡ “እስራኤል ሆይ፥ ስማ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው ፡፡ አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ ውደድ። ዘዳ 6፥5
            “በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም ኃይልህ እግዚአብሔርን ውደድ ” የሚለው ቃል፤ እግዚአብሔርን ለመውደድ ፍፁም ልብ እንደሚያስፈልግ  ያስረዳል፡፡ ሀሳብ እና ፍቅር መኖሪያቸው ልብ ነው፡፡ ፍጹም ልብ ወደ አንድ ሀሳብ ሲመራ፤ አንድ ሀሳብ ደግሞ ወደ ፍጹም ነፍስ እና ኃይል  ያደርሳል፡፡ ስሊህም በልባችን እግዚአብሐርን እንወዳለን፡፡ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ በልባችን በአንድ ሀሳብ እግዚአብሔርን በምንወድበት ጊዜ ባልንጀራችንንም እንደምንወድ አስተምሮናል፤ እንዲህ በማለት  ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።
እነዚህ ሁለት ትእዛዛት ማለትም እግዚአብሔርን መውድ እና ባልንጀራን መውደድ በአንዱ ልባችን ውስጥ በአንድ ሀሳብ በፍቅር ይጠቃለላሉ፡፡ ሁለተኛይቱ ትእዛዝ የታላቁ ትእዛዝ አካል በመሆኗ የማይነጣጠሉ ፍቅርን መሰረት ያደረጉ አንድ ሀሳብ ናቸው፡፡ ፊተኛይቱ ታላቁ ትእዛዝ እግዚአብሔርን በፍጹም ፍቅር መውደድ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የሆነ ፍቅር የለም ቢኖር እንኳን ኃጢአት ነው፡፡ ስለዚህም ታላቂቱ እና ፈተኛይቱ የተባለችው ከእርሷ የሚያንሱ እንጂ የሚበልጡ ስለሌሉ ነው፡፡ እንዲሁም ከእርሷ የሚከተሉ እንጂ የሚቀድሙ ባለመኖራቸው እግዚአብሔርን ከመውደድ የሚበልጥ የሚቀድም ነገር ምንም አይኖርም፡፡
ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለሚገኙ ሁለት አይነት ሰዎች እውነተኛውን ምላሽ እንዲሰጡ በጥብቅ አሳስበን የሚከተለውን ጥያቄ እናቅረብላቸው፡፡ በስዕለት ወንድ ልጅ ለወለደችው እናት እንዲህ እንበላት “እውነቱን ተናገሪ ከልጅሽ እና ከእግዚአብሔር ማንን ትወጃለሽ?” ብለን ብንጠይቃት፡፡ እንደዚሁም ለማግባት ጥቂት ቀናት የቀረውን ሙሽራ “በጣም ከምትወዳት ከእጮኛህ እና ከእግዚአብሔር ማንን ትወዳለህ ? ” ተብሎ ጥያቄ ቢቀርብለት ምን አይነት ፈታኝ እና ከባድ ጥያቄ ቀረበልን ካሉ በኋላ መልሳቸው እንደዚህ ይሆናል፡፡ ወንድ ልጅ በስዕለት ያገኘችው እናት መልሷ “ ልጄን ነው የምወደው ” ከሆነ፡፡ እንደዚሁም “ጎልማሳ በሚስቱ እንዲሉ” የሙሽራውም መልስ “እጮኛዬን” ከሆነ ፤ ከሰጪው ከእግዚአብሔር ይልቅ ስጦታውን አብልጠው ወደዋል እና ኃጢአት ይሆንባቸዋል፤ ምክንያቱም የፊተኛይቱን ትእዛዝ የሆነችው እግዚአብሔርን መውደድ ከማንኛውም እና ከምንም አስቀድሞ ፣ አስበልጦም ጭምር በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን መውድ ስለሆነ ፡፡ ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ ከእግዚአብሔር አስበልጠን የምንወደው እንደሌለን ሲያስተምረን  “ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤” ብሎአል፡፡ማርቆስ 10፥37  ነገር ግን እግዚአብሔር ለእርሱ ካለን ፍቅር ይልቅ ሌሎችን ካስበለጥን ልባችን ወደ እርሱ እስኪመለስ ድረስ ይተወናል እንጂ ፈጽሞ አይጠላንም፡፡ ይህንንም አስደናቂ የእግዚአብሔር ፍቅር ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ እንዲህ በማለት ገልጾታል “እግዚአብሔር ከሚወደው ሰው ይልቅ እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ያስደንቀኛል” ብሎአል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍቅር ከባሕሪው የሚገኝ ነውና፡፡
ፈተኛይቱ ትእዛዝ በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን መውድ ነው፡፡ ሀሳባችንን ለማንም ሳናስቀድም ለእግዚአብሔር ብቻ መስጠት ነው፡፡ ራስ ካሳ ፍኖተ አእምሮ በተሰኘው መጽሐፋቸው “እግዚአብሔርን መውደድ ማለት የምትወደውን ነገር ማናቸውንም ነገር ቢሆን ለእኔ ይቅርብኝ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይሁንልኝ ብለህ፤ ቢቻልህ ጨርሰህ፤ ባይቻልህ ከፍለህ የምትወደውን መስጠት ነው” ብለዋል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን መውደዳችን የሚታወቀው በአንደበታችን በምናደርገው ንግግር ሳይሆን በሙሉ ልብ ለእግዚአብሔር በመታዘዛችን እና ስለእርሱ ፍቅርም በምንከፍለው መሥዋዕትነት ነው፡፡
 “ አንድ ሀሳብ ይሁንላችሁ፤” የሚለው ቃል እግዚአብሔር በአንድ ሀሳብ በፍጹም ኃይል ልንወደው እንደሚገባ ያስረዳል፡፡ በተረት “አንዱን ይዞ ፤አዱን አንጠልጥሎ” እንዲሉ በአንድ ልብ ሁለት ሀሳብ፤ ሁለት ፍቅር አይቻልም፡፡ አባቶቻችንም “ሁለት ልብ ያለው ሁሌም የታወከ ነው ” እንደ ሚሉት በሁለት ሀሳብ ሲዋልል ይኖራል፡፡ ቅዱስ ወንጌልም ይህንን ሲያረጋግጥልን ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ” ማቴ 6•24 የሚለን፡፡ ስለዚህ ዓለምንም እግዚአብሔርንም እንደ አስፈላጊነቱ እየለዋወጡ መውደድ አይቻልም፤ ምክንያቱም ፍቅር  በአንድ  ልብ ነውና፡፡
የተከፋፈለ ልብ ፈጽሞ አንድ ፍቅር የለውም፡፡እንዲህ አይነት ልብም ይዘን እግዚአብሔርን እንወዳለን እናመልካለን ብለን መናገራችን እንኳን ድፍረት ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር የሚወደው እና የሚፈልገው በአንዳች ነገር ያልተከፋፈለ አንድ የፍቅር ልብ ነው፡፡ ሰውም ቢሆን ፣ ገንዘቡም ቢሆን በዓለሙ ውስጥ ያለው ወርቁም ብሩም ቢሆን በፍጹም ፍቅር ልንወደው አይገባንም፡፡ እግዚአብሔርን የምናመልክበትን እና የምንወድበትን ልባችንን ሊቆጣጠረውም ወይም አብላጫውን ቦታ ከፍለን ልንሰጠው አይገባም፡፡ ይህን ያደረግን እንደሆነ ለእግዚአብሔር መገዛት አንችልም ፡፡ በዚህም የተነሳ የፊተኛይቱን ትዕዛዝ እንሽራለን፡፡ የመጀመሪያይቱን ትእዛዝ በፍጹም ልብ እግዚአብሔርን መውደድ ዘላለማዊ ሲሆን የተቀረው ፍቅር ግን ጊዜያዊ ነው፡፡ዛሬ በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ትልቁ ደዌያችን የተከፋፈለ ፍቅር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በልባችን ያለው ሥፍራ እጅግ ጠቦ በጊዜያዊው ዓለም ሀሳብ ተጣቧል፡፡እግዚአብሔርንም ዓለምንም መውደድ እንፈልጋለን፤ ስለ እግዚአብሔርም ስለ ዓለምም እናስባለን፡፡
በፍጹም ልባችን እግዚአብሔርን ያመለክን እንደሆነ ሌሌች ሰዎችን እንዴት መውደድ እንችላለን ለሚለው ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን፡፡ ሌሎቹን ሁሉ የምንወደው በእግዚአብሔር ፍቅር መሰረትነት ነው፡፡ ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት። በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል።” እንደተባለ፡፡  ሐዋርያው ዮሐንስ በመልእክቱ እንዲህ ይላል “ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ። ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።” 1ኛ ዮሐ 48  እንደዚሁም በሌላ መልእክቱ “እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።”1ኛ ዮሐ 4፥16 በማለት ያስተምራል፡፡
ፍቅር ሁለት ልቦችን አንድ ሀሳብ ማድረግ ነው፡፡ ወይም ሁለት ልቦችን በተመሳሳይ ስሜት እና ፍላጎት ሀሳብ ማስተሳሰር ነው፡፡ ይህም የተቀደሰ ፍቅር ይሆናል፡፡ ስሜቱም በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ የተመሰረተ ከሆነ ከእርሱ ጋር የማይጋጭ የማይበልጥ መንፈሳዊ ፍቅር ነው፡፡ባልንጀራችንንም ስንወድ በዚህ መርህ መሰረት ነው፡፡
ፍቅር ሳይኖረን ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት ብንፈጽም ከንቱ ድካም ይሆንብናል ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም “ትንቢትም ቢኖረኝ ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ። ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፥ ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም”። 1ኛ ቆሮ 13፥ በማለት ተናግሮአል፡፡ መንፈሳዊ ሕይወታችንን ፣ ኑሮአችንን አገልግሎታችንን ሁሉ  በአንድ ፍቅር  ፣ በአንድም ልብ፣  በአንድም አሳብ እናድርግ፡፡ በዚህ እግዚአብሔርን መውደዳችን ይታወቃል፡፡ እግዚአብሔርም ከእኛጋር ይሆናል፡፡
ይቆየን
ያዕቆብ ሰንደቁ
ግንቦት 13 2008
አዲስ አበባ