ቤተልሔም፡ የትንቢት መፈጸሚያ
በይሁዳ
ምድር ካሉ
ኮረብታዎች መካከል
አንዷ በሆነችው
ቤተልሔም ላይ
ቆመን ወደ
ኋላ ዘመናትን
ብንቃኝ፣ ዓለምን
የቀየሩ ታላላቅ
ክስተቶች በዐይነ ህሊናችን ይታያሉ። ቤተልሔም ዝምተኛ
ከተማ ብትመስልም፣
አፈርዋ ግን
የነገሥታትን ደም፣
የአርበኞችን ላብና
የቅዱሳንን ጸሎት
አቅፋ የያዘች
የታሪክ ሙዚየም
ናት።
ከኢየሩሳሌም
በስተደቡብ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቃ የምትገኘው ቤተልሔም፣ ስሟ ሲተረጎም "የእንጀራ ቤት" ማለት ነው። ይህች
ከተማ በቆዳ ስፋቷ አነስተኛ ብትሆንም፣ በውስጧ የያዘችው የታሪክ ክምችት ግን ዓለምን የለወጠ እና ያዳነው ነው። እስኪ የዚችን ከተማ አውራ ጎዳናዎች እና ዋሻ በታሪክ
መነጽር እንቃኛቸው።
1.
የራሔል መቃብርና የቤተልሔም ጥንታዊነት
የቤተልሔም ከተማ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎልቶ የሚወጣው በሐዘን ታሪክ ነው። አባታችን ያዕቆብ ወደ ኬብሮን በሚጓዝበት ወቅት፣ የምትወደው ሚስቱ ራሔል በምጥ ተይዛ በቤተልሔም (ኤፍራታ) አቅራቢያ አረፈች። “ራሔልም ሞተች፥ ወደ ኤፍራታ በሚወስደውም መንገድ ተቀበረች እርስዋም ቤተ ልሔም ናት።” (ዘፍጥረት 35:19) ያዕቆብም በመቃብሯ ላይ የሐውልት ድንጋይ አቆመ። ይህ ክስተት ቤተልሔም ከክርስቶስ ልደት በብዙ ሺህ ዓመታት በፊት የታወቀች ስፍራ መሆኑዋን ያሳየናል። እስከ ዛሬ ድረስ ይህ መቃብር የአይሁድ፣ የክርስቲያንና የሙስሊም ተጓዦች የሚጎበኙት የታሪክ ምልክት ነው።
2.
የሩትና የቦዔዝ የፍቅር ታሪክ፡
ወደ መሳፍንት ዘመን ስንመለስ፣ ቤተልሔም
የአንዲት ሞአባዊት ሴት የጽናት ታሪክ መድረክ ሆና እናገኛታለን። ቤተልሔም "የእንጀራ ቤት" የተባለችው በከንቱ አይደለም። በሩት መጽሐፍ ውስጥ እንደምናየው፣ በምድሪቱ ላይ ረሃብ በነበረበት ወቅት ቤተልሔም የተስፋ ምድር ነበረች። ሞአባዊቷ ሩት አማቷን ናኦሚን ተከትላ ወደዚች ከተማ በመጣች ጊዜ፣ በቦዔዝ የእርሻ ማሳ ውስጥ ቃርሚያ ስትሰበስብ ያገኘችው በረከት ለታላቁ የዳዊት የትውልድ ግንድ መገኛ ሆነ። ይህ ታሪክ ቤተልሔም የሰው ልጅ ዘርና ጎሳ ሳይለይ እግዚአብሔር ለሁሉ ጸጋውን የሚሰጥባት ስፍራ መሆኗን ያበስራል።
3. የዳዊት ከተማና የቅብዐት ምስጢር
ቤተልሔም በታሪክ መዝገብ ላይ በደመቀ ቀለም የተጻፈችው ግን በንጉሥ ዳዊት ምክንያት ነው። እረኛው ዳዊት በቤተልሔም ሜዳዎች ላይ በጎቹን እየጠበቀ በበገናው እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ነቢዩ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ እሴይ ቤት በመጣ ጊዜ፣ ከታላላቆቹና ቁመና ካላቸው ወንድሞቹ ይልቅ፣ በቤተልሔም ሜዳ ላይ በግ የሚጠብቀው ታናሹ ዳዊት ለእስራኤል ንጉሥነት ተቀባ።“ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ
በወንድሞቹ መካከል ቀባው፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ።” (1 ሳሙኤል 16:13)
ቤተልሔም "የዳዊት ከተማ" የተባለችውም ዳዊት የተወለደባት፣ ያደገባትና የተቀባባት በመሆኗ ነው። የዳዊት ወታደሮች ሳይቀሩ "ከቤተልሔም በበር አጠገብ ካለው ጉድጓድ ውሃ ማን በሰጠኝ!" ብለው የሚናፍቋት የተባረከች ስፍራ ነበረች።
4.
የትንቢቱ ፍጻሜ፡ የዓለም መድኃኒት ልደት
ይህች ትንሿ ከተማ የዓለም ትኩረት የሆነችው ግን የነቢያት ትንቢት ሲፈጸምባት ነው። ነቢዩ ሚክያስ ከሰባት መቶ ዓመታት በፊት "አንቺ ቤተልሔም... ከአንቺ እስራኤልን የሚገዛ ይወጣል" (ሚክያስ 5:2) ብሎ የተነበየው ትንቢት በግርግም ውስጥ ተፈጸመ።
የሮማው
ንጉሥ አውግስጦስ
ቄሳር ባወጣው
የሕዝብ ቆጠራ
ትዕዛዝ ምክንያት፣
ዮሴፍና ማርያም
ከናዝሬት ተነስተው
ወደ ትውልድ
ከተማቸው ቤተልሔም
መጡ። በዚያም
የእንግዳ ማረፊያ
ቦታ በመጥፋቱ፣
በቤተልሔም ዋሻ
ውስጥ የዓለም
ብርሃን ተወለደ።
ያን ዕለት
የቤተልሔም እረኞች
የመላእክትን የምስራች
የሰሙባት፣ ሰብአ
ሰገልም ከሩቅ
ምስራቅ በኮከብ
ተመርተው ወርቅ፣
እጣንና ከርቤ
ያቀረቡባት ድንቅ
ከተማ ሆነች።
5. ዮሴፍና ማርያም፡ ወደ ትውልድ ስፍራ ጉዞ
ምንም እንኳን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደገው በናዝሬት
ቢሆንም፣ የዮሴፍና የማርያም የትውልድ ሥር ከቤተልሔም (ከዳዊት ቤት) ጋር የተሳሰረ ነው። ሉቃስ 2:4 ላይ እንደሚነግረን፣ ዮሴፍ ከዳዊት ወገንና ቤት ስለነበረ "የዳዊት ከተማ ወደምትሆን ወደ ቤተልሔም" ወጣ ይላል። ይህ ጉዞ ቤተልሔም የቤተሰብ ሥርና የቃል ኪዳን መገኛ መሆኗን ያረጋግጣል።
ዛሬ ቤተልሔም ምን ትመስላለች?
በአሁኑ ወቅት ቤተልሔም በዓለም ላይ ካሉ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የሆነውን የልደት ቤተክርስቲያንን (Church
of the Nativity) በጉያዋ
ይዛለች። በሚሊዮን የሚቆጠሩ መንገደኞች በየዓመቱ የክርስቶስን የልደት ስፍራ ለመሳለምና የታሪኩ ተካፋይ ለመሆን ወደዚህች ከተማ ይተማሉ። ቤተልሔም
ዛሬም እንደ
ጥንቱ የዓለም
መንፈሳዊ መካነ
ህብስት ሆኖም ግን
የዛሬዋ ቤተልሔም
የመጽሐፍ ቅዱስ
ታሪክ ብቻ
ሳትሆን፣ የፖለቲካ፣
የቱሪዝም እና
የበርካታ አብያተ
ክርስቲያናት መገናኛ
ነጥብ ናት።
1. የጌታ ልደት አከባበር በቤተልሔም
በቤተልሔም የጌታ ልደት (ገና) አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሦስት ጊዜ ነው የሚከበረው። ይህም በከተማዋ ባሉ የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የዘመን አቆጣጠር ምክንያት ነው፡-
·
ታኅሣሥ
25 (December 25):
በካቶሊክ እና
በፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት።
·
ታህሳስ 29 (January 7): በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣
በግብፅ ኮፕቲክ፣ በግሪክ እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት።
·
ጥር
19 (January 19):
በአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን።
በእነዚህ ቀናት የከተማዋ ማዕከል የሆነው የማንገር አደባባይ
(Manger Square)
በሺዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ይሞላል። የልደት ዋሻ በሚገኝበት "የልደት ቤተክርስቲያን" ውስጥ ታላላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓቶች ይከናወናሉ። በተለይም በታኅሣሥ 24 ምሽት የሚደረገው የቅዳሴ ጸሎት በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በቴሌቪዥን በቀጥታ ይከታተሉታል።
2.
በቤተልሔም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት
ቤተልሔም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የሚታይባት ስፍራ ናት። ዋና ዋናዎቹም፡-
·
የልደት ቤተክርስቲያን (Church of the Nativity): በዓለም ላይ ካሉ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ሲሆን፣ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት ተመዝግቧል። ይህ ቤተክርስቲያን በጋራ በግሪክ ኦርቶዶክስ፣ በአርመን ኦርቶዶክስና በሮማ ካቶሊክ ቁጥጥር ስር ነው።
3.
አይሁድ የቤተልሔም ከተማዋን
እንዴት ያዩታል?
ለአይሁድ
ቤተልሔም ታሪካዊቷ
የንጉሥ ዳዊት
ከተማ ናት።
ሆኖም ግን
በአሁኑ ሰዓት
ቤተልሔም በፍልስጤም
አስተዳደር ስር
የምትገኝ በመሆኗ፣
የእስራኤል ዜግነት
ያላቸው አይሁድ
ወደ ከተማዋ
በነፃነት መግባት
በሕግ ተከልክለዋል።
አይሁድ
ከከተማዋ መግቢያ
ላይ የሚገኘውን
የራሔልን መቃብር በከፍተኛ
ሁኔታ ያከብራሉ።
ይህ ስፍራ
በእስራኤል ወታደራዊ
ጥበቃ ስር
ስለሆነ አይሁድ
በብዛት መጥተው
ይጸልዩበታል። ነገር
ግን ወደ
ከተማዋ መሃል
መግባት ለደህንነታቸው
አስጊ እንደሆነ
ስለሚታሰብና በፖለቲካዊ
ውጥረቱ ምክንያት
ግንኙነቱ ውስብስብ
ነው።
4.
የቱሪስቶች ብዛት
ቤተልሔም
ኢኮኖሚ በቱሪዝም
ላይ የተመሰረተች
ከተማ ናት።
· የቱሪስት
ብዛት: በየዓመቱ በአማካይ
ከ 1.5 ሚሊዮን እስከ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ
ቱሪስቶች ቤተልሔምን
ይጎበኛሉ። በተለይ
በገና ወቅት
ሆቴሎች ሙሉ
በሙሉ ይያዛሉ።
· የእደ
ጥበብ ውጤቶች: ከተማዋ በወይራ
እንጨት በሚሠሩ
ቅርጻ ቅርጾች
(መስቀል፣ በረት፣
ቅዱሳን ሥዕላት)
ትታወቃለች። ይህ
የከተማዋ ነዋሪዎች
ዋና የገቢ
ምንጭ ነው።
5.
የወቅቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ
ቤተልሔም
ዛሬ ከእስራኤል
ከተሞች በግዙፍ
የኮንክሪት ግድግዳ ተለይታ
ትገኛለች። ወደ
ከተማዋ ለመግባትና
ለመውጣት በእስራኤል
ወታደሮች የሚጠበቁ
ኬላዎችን ማለፍ
ግድ ይላል።
ይህ ሁኔታ
በነዋሪዎች እንቅስቃሴና
በቱሪዝሙ ላይ
አንዳንድ ጊዜ
ተጽዕኖ ያሳድራል፤
ሆኖም ቱሪስቶች
በሰላም ገብተው
እንዲወጡ ከፍተኛ
ጥበቃ ይደረጋል።
6 .ጌታ የተወለደበት ዋሻ
"ጌታ
የተወለደው እዚህ
ነው" ተብሎ ለሚታመነው
ስፍራ (የልደት
ዋሻ) እንደ
ማረጋገጫ የሚጠቀሱ
የታሪክ እና የመንፈሳዊ
ተአምራት ማስረጃዎች
አሉ።
የታሪክና
የትውፊት ማረጋገጫ
ጌታ በተወለደ በአጭር
ጊዜ ውስጥ
(ከ100 ዓመታት
ባነሰ ጊዜ)
ያ ስፍራ
በክርስቲያኖች ዘንድ
ይታወቅ ነበር።
· ቅዱስ
ዩስጢኖስ: በ150 ዓ.ም አካባቢ
(ኢየሱስ በተወለደ
በ150 ዓመቱ)
ጌታ የተወለደው
በቤተልሔም አቅራቢያ
ባለ ዋሻ
ውስጥ እንደሆነ
ጽፏል።
· ኦሪገን:
በ248 ዓ.ም ቤተልሔምን
በጎበኘበት ወቅት፣
በከተማዋ ያሉ
ሰዎች ሁሉ
ጌታ የተወለደበትን
ዋሻ እንደሚያውቁና
አህዛብ (ሮማውያን)
እንኳ ሳይቀሩ
ስፍራውን ለይተው
እንደሚያውቁት መስክሯል።
የአፄ ቆስጠንጢኖስና
የእናቱ የንግሥት ዕሌኒ ምስክርነት
በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን
ንግሥት ዕሌኒ
ወደ ኢየሩሳሌም
በመጣች ጊዜ፣
የአካባቢው ሰዎች
ጥንት ጀምሮ
ሲጠብቁት የነበረውን
የልደት ዋሻ
አሳዩዋት። በ326
ዓ.ም
በዚህ ዋሻ
ላይ የመጀመሪያው
የልደት ቤተክርስቲያን (Church of the Nativity)
ተሠራ። የሚገርመው
ነገር፣ ከዚያ
ዘመን ጀምሮ
እስካሁን ድረስ
ቤተክርስቲያኑ በተለያዩ
ጦርነቶች ቢፈርስም፣
ዋናው መሠረትና
ዋሻው ግን
ሳይነካ ጸንቶ
ቆይቷል።
የሚታይ ድንቅ
ምልክት፡ የብር ኮከቡ
በዋሻው ውስጥ ጌታ ተወለደ ተብሎ በሚታመነው ትክክለኛ ስፍራ ላይ የብር ኮከብ ተቀምጧል። ይህ ኮከብ 14 ጨረሮች አሉት።
· ምልክቱ፡ 14 ጨረሮች ያሉት
መሆኑ ከማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ላይ ያለውን የጌታን የትውልድ ግንድ (ከአብርሃም እስከ ዳዊት 14፣ ከዳዊት እስከ ባቢሎን 14፣ ከባቢሎን እስከ ክርስቶስ 14 ትውልድ) ለመወከል ነው።
· ጽሑፉ፡ በኮከቡ
ላይ በላቲን ቋንቋ "Hic de
Virgine Maria Jesus Christus Natus Est" (እዚህ ከድንግል ማርያም ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ) የሚል ጽሑፍ ተቀርጾበታል።
7
ተአምራዊው "የወተት ዋሻ"
ከዋሻው ጥቂት
ሜትሮች ርቆ
የሚገኝ ሌላው
ድንቅ ምልክት
"የወተት ዋሻ"
ነው። ትውፊቱ
እንደሚነግረን እመቤታችን
ሕፃኑን ስታጠባ
የወተት ጠብታ
በድንጋዩ ላይ
በመፍሰሱ፣ ቀይ
የነበረው የዋሻው
ድንጋይ ወደ
ነጭነት ተቀይሯል።
· ተአምራቱ፡
ዛሬም ድረስ
መካን የሆኑ
ሴቶች (ክርስቲያኖችም
ሙስሊሞችም) ከዚህ
ነጭ ድንጋይ
ላይ የተፈጨውን
ዱቄት በእምነት
በመውሰድ ልጅ
እንደሚወልዱ ይነገራል፤
ለዚህም ምስክር
የሆኑ በሺዎች
የሚቆጠሩ የልጆች
ፎቶዎች በቤተክርስቲያኑ
ግድግዳ ላይ
ተለጥፈው ይታያሉ።
ድንቅ የታሪክ
ክስተት (የፋርስ ወራሪዎች)
በ614
ዓ.ም
ፋርሶች (ፐርሺያ)
ፍልስጤምን በወረሩ
ጊዜ በየቦታው
ያሉ አብያተ
ክርስቲያናትን አቃጥለው
ነበር። ሆኖም
የቤተልሔምን የልደት
ቤተክርስቲያን ለማጥፋት
ሲገቡ፣ በግድግዳው
ላይ የተሣለውን
የሰብአ ሰገልን ሥዕል ተመለከቱ።
ሰብአ ሰገል
የፋርስ ልብስ
(የራሳቸውን ሀገር
ልብስ) ለብሰው
ስለነበር፣ ፋርሶቹ
ሥፍራውን አክብረው
ሳይነኩት ወጥተዋል።
ይህ ለቤተክርስቲያኑ
መትረፍ እንደ
ትልቅ ተአምር
ይታያል።
ወደ ዋሻው
ውስጥ የገባ
ማንኛውም ሰው
የሚሰማው ልዩ
ሰላምና መንፈሳዊ
ኃይል አለ።
ዋሻው ጠባብና
ዝቅ ያለ
በመሆኑ፣ ወደ
ስፍራው የሚገባ
ሁሉ ጎንበስ
ብሎ (በትሕትና)
መግባት አለበት።
ይህም የጌታን
ትሕትና የሚያስታውስ
ድንቅ ምልክት
ነው።
በበረት ተኛ በጨርቅ ተጠቀለለ የዓለም መድኃኒት በቤተልሔም
ተወለደ።
