የዕድል ፈንጠዚያ 💔
አቶ ቶማስ ሮሲ ለባለቤቱ ለዴኒዝ የነበረው ፍቅር ለብዙዎች አርአያ የሚሆን ነበር። ቶማስ ለሚስቱ የማይሆንላት ነገር የለም።
ኑሯቸው እንዲሻሻል፣ ቤታቸው በደስታ እንዲሞላ ፤ ሌት ተቀን በሥራ ይተጋል። ምንም እንኳን የሥራው ብዛት ከቤተሰቡ ጋር የሚያሳልፈውን ጊዜ ቢቀንስበትም፣ ዓላማው ግን አንድ ብቻ ነበር— ለሚስቱ የተሟላና የተንደላቀቀ ኑሮ መመሥረት߹ ትዳሩን መገንባት።
ዴኒዝም በበኩሏ ከቶማስ ጋር በፍቅርና በሰላም የምትኖር ትመስል ነበር። ነገር ግን በአንድ ወቅት ቶማስ በሥራ መወጠሩን እንደ ምክንያት በማንሳት "ጊዜ አልሰጠኸኝም" የሚል ቅሬታ ማቅረብ ጀመረች። ቶማስ ሁኔታውን ለማስተካከል ውድ ሥጦታ በመግዛት߹ ጊዜ በመስጠት߹ ከበፊቱ የበለጠ እንክብካቤ በለማድረግ ሞከረ፣ ነገሮች ግን እርሱ ካሰበው በተቃራኒ አቅጣጫ መጓዝ ጀመሩ።
በጥር ወር ቶማስ ጨርሶ ሊገምተው የማይችለው ነገር ተከሰተ። ዴኒዝ አንድ ቀን ጠዋት ፊት ለፊቱ ቆማ "ከእንግዲህ ካንተ ጋር መኖር አልፈልግም፤ ትዳራችን በፍጥነት እንዲፈርስ ወስኛለሁ" ስትል አረዳችው።
ቶማስ ክንፉና እግሩ እንደተሰበረ እርግብ ስብስብ ብሎ ተንገዳገደ አቅም አነሰው ደነገጠ። "ምንድነው ጥፋቴ? ምንድነው ያጎደልኩብሽ? ተረጋግተሽ አስቢበት" እያለ ይማጸናት ጀመር ዴኒዝ ግን መስማት አልፈለገችም በጩኸት ከ አንተጋር መኖር አልፈልግም አለች።
በማግስቱ በከፍተኛ ፍጥነትና ብልጠት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዳ፣ በብዙ ድካም የተመሰረተውን ቤት߹ በቀላል ምክንያት የምታፈርስበትን ሁኔታ አመቻችታ የተለፋበትን የትዳር ጎጆ ፤እንደ ዋዛ በፍርድ ቤት አፍርሳው አረፈች። ቶማስም በሐዘን ተሰብሮ፣ በብቸኝነት߹ጭንቀት ተውጦ ሁሉንም ነገር ትቶላት በባዶ እጁን በባዶ ቤት ለመኖር ተለያት።
ከፍቺው ሁለት ዓመት በኋላ አንድ ቀን ቶማስ ብቻውን በቤቱ ቁጭ ብሎ መጽሐፍ እያነበበ በሩ ተንኳኳ። አንድ የፖስታ መልእክተኛ በስህተት ለቀድሞ ባለቤቱ የተላከን ደብዳቤ ሰጥቶት ሄደ። ቶማስ ደብዳቤውን ሲከፍተው ግን ዓይኑን ማመን አቃተው! መላ ሰውነቱ በድንጋጤ እንደበረዶ ቀዘቀዘ።
ዴኒዝ ፍቺ ከመጠየቋ ከ11 ቀናት በፊት የ1.3 ሚሊየን ዶላር ባለቤት ሆና ነበር!
ይህች ሴት ለዓመታት አብሯት የለፋውን፣ የወደዳትንና የተንከባከባትን ባሏን "ገንዘብ አላካፍልም" በማለት፣ ሚሊየነር መሆኗን ደብቃ በጭካኔ ፈትታው ኖሯል። ፍቺ የጠየቀችው ስለተበደለች ሳይሆን፣ ያገኘችውን በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ለብቻዋ ለመጠቀም አስባ ነበር።
አቶ ቶማስ ወዲያውኑ የካሊፎርኒያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ መዝገብ ከፈተ። ዳኛ ሪቻርድ ዴነር ጉዳዩን ሲመረምሩ በዴኒዝ ተንኮል እጅግ አዘኑ። ዴኒዝ በፍርድ ቤት "ሎተሪው የደረሰኝ ለእኔ ስለሆነ፤ ገንዘቡ የኔ የግል ብቻ ስስመሰለኝ ነው" ብላ ብታብራራም፣ ዳኛው ግን በሕጉ መሠረት ጥብቅ ውሳኔ አስተላለፉ፦
"ዴኒዝ ሆይ! በሐቀኝነት ብትናገሪ ኖሮ የገንዘቡን ግማሽ ($668,000) በሕግ ትወስጂ ነበር። ነገር ግን የትዳር አጋርሽን ለማታለልና ድርሻውን ለመንፈግ ስላሴርሽ፣ እንደ ቅጣት ሙሉው 1.3 ሚሊየን ዶላር ለተበዳዩ ባል ለቶማስ እንዲሰጥ ወስኛለሁ!"
ዴኒዝ ሁሉንም ለብቻዬ ልውሰድ ስትል፣ ሕጋዊ ድርሻዋን ጭምር አጥታ በባዶ እጇ ቀረች። ቶማስ ግን በታማኝነቱና በመከራው ምክንያት ሳይገምተው የሚሊየነርነት ካባ ደረበ።
+++++

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ