ሰኞ 11 ኤፕሪል 2016

ወግ በስም ስህተት ነው



ክፍል ሁለት
እመት አይጠግቤ
      የአካባቢው ሰው እመት አይጠግቤ እያለ ይጠራቸዋል፡፡ የሚኖሩት ብቻቸውን ሻንቆ ከተባለው ውሻቸው ጋር ነው፡፡ ከመንደሩ ሰው ከጎረቤቱ ቀዬዉ፣ ካሳሩ ከቅጠሉ ጋር አይስሙም፤ ቤተ ክርስቲያን አይሄዱ ፣ያዘነ አያጽናኑ የታመመ አይጠይቁ፤ በር ፣ጽዋ አይጠጡ ብቻቸውን ይውላሉ ያድራሉ፡፡ ጭካኔያቸው ወሰን ዳር ድንበር የሌለው፤ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ነው ፡፡
      የሀገሬው ሰው እንደሚያወራው አንዱን በዝ ገበሬ ከሚስቱ ቀምተው በመድኃኒት አፍዝዘው ጉልበቱን እየበዘበዙ አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ ከዚያም ንብረቱን እና ከብቶቹን ሁሉ ሸጦ የቀደመ ትዳሩን እንዲበትን አስገደዱት፡፡ ንብረቱንም ለመዝረፍ ቤትህንም እናቃጥለው እያሉ ያስጨንቁት ጀመር፡፡ አሳባቸውን በመቃወሙ ሊገድሉት ጊዜ ይጠብቁ ጀመር፡፡
     እመት አይጠግቤ ከገበሬው ጋር ተያይዘው ገበያ ሲሄዱ፤ ቀኑ ጭጋጋማ ነበር ጉም ጋርዶት አዳልጦት ወደቀ እገደል ጫፍ ተንጠልጥሎ “እጅሽን ዘርግተ አድኝኝ ቢላቸው ወደ ገደል ገፍትረው ወረወሩት፡፡ ሰባራ ሳንቲም የወደቀባቸው ሳይመስላቸው ባላቸውን ገደል ጨምረው ወደ ታቸው ተመለሱ፡፡ ፀሐይ ወጥቶ ደመናው ገፈፈ፡፡ ከገበያ የተመለሱ ሰዎች የደሙን እንጥብጣቢ ተመለከቱ፡፡ ቁልቁል ወርደው ገደል የገባውን ገበሬ አግኝተው ከገደሉ አውጡት፡፡ በበቅሎ ጭነው ወደ ጤና ኬላ መጡ፡፡ ብዙ ስለፈሰሰው ሕይወቱ አለፈ፡፡ ቤተሰቦቹም በሀዘን ልባቸው ተሰብሮ ሬሳውን ወስደው ቀበሩ፡፡ ወዲያውኑ ለፖሊስ በማመልከታቸው ሁኔታውን ለማጣራት እና ለምርመራ ለሦስት ወራት እመት አይጠግቤ ታሰሩ ገበሬው የሞተው መንገድ ስቶ ገደል ገብቶ እንጂ በእርሳቸው ተገፍትሮ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ አልተገኘም፡፡ ለው በነጻ ለቀቸው፡፡ የመንደሩ ሰው የሰው ሚስት መቀማ ሳያንስ አፍዝዛ ገደለችው እያለ ከበፊቱ አብልጦ ጠላቸው፣ አራቃቸው፡፡
     ወሕይኒ ቤት ከተለቀቁ ከቀድሞው የበለጠ ከሰው ተገለሉ፤ የሚጎዙት በሌሊት ሲሆን በዱሩ፣ በጫካው ፣በበረሀው ሁሉ ይውላሉ ያድራሉ፡፡ የሚወርሳቸው ልጅ ወይም ዘመድ የላቸውም፡፡ ብዙ ገንዘብ ለመሰብሰብ አይጠግቡም፤ በሌሊት ተነስተው የጎረቤት ክምር ይዘርፋሉ፤ የሰው ጎተራ ሰብረው ይሰርቃሉ፡፡ ይህንንም ተግባር የሚፈጽሙት ሆን ብለው በተን ከተሞላው ልባቸው አመንጭተው ነው፡፡ የሚጠሉት ሰውን ብቻ አይደለም እንስሳትንም በጣም ይጠላሉ፤ በመንገድ ላይ የበግም ይሁን የፍየል ግልገል ካገኙ ከእናቲቱ ነጥለው ይወስዳሉ፡፡ በመንደሩ ዙሪያ ገባ አዲስ የተወለደ የድመት ብጭሊት የውሻ ቡችላ ካገኙ ወደ ገደል ፈጥፍጠው ይገላሉ፡፡
     ከአባቴ ተምሬዋለሁ የሚሉት የባህል ክምና እውቀት አላቸው፡፡ የአካባቢው ሰው ዛር መንፈስ አለባቸው ጋኔን ሰፍሮባቸዋል ጠንቋይ ናቸው ይላቸዋል፡፡ ከማንኝውም ሰው ጋር ተግባቦት ባይኖራቸውም ሕፃናት እና ሴትን ግን ማየትን አይወዱም፡፡ ሲያሰኛቸው ተማተው ካልሆነላቸውም ደግሞ አስፈራርተው ከአጠገባቸው ያባርራሉ፡፡ ከመኖሩያቸው ርቆ በሚገኘው ገበያ አካባቢ ባለች አንዲት ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ከሳምንቱ የተወሰነ ቀናት ያሳልፋሉ፡፡ ለልዩ ልዩ በሽታዎች የሚሆን ባሕላዊ መድኃኒቶች እጽዋት እና ከአራዊት ስለሚቀምሙ ከሩቅ ሀገር ድረስ እየመጡ መድኃኒቱን በውድ ዋጋ ስድብ እና ግልምጫ ታክሎበት ይገዛሉ፡፡ 
     ከልዩ ልዩ ቦታ ለሚመጡ ሴቶች ብዙ ገንዘ አስከፍለው ንስ ያስወርዳሉ፡፡ በዚህ በኃጢአት ሥራ በየጊዜው ብዙ ገንዘብ ይሰበስባሉ፡፡ ሴቶቹ ሊከፍሉት ይዘውት ከመጡት ገንዘብ በተጨማሪ የአንገታቸውን ሀብል፣ የጣታቸውን ቀለበት፣ የዕጃቸውን አንባር ይዘርፋሉ፡፡ የዘረፉትን ጌጣጌጥ እና ያገኙትን ገንዘብ በማዳበሪያ እየሰፉ ፍራሽ እና ትራስ አድርገው ይተኙበታል፡፡ 
     ከአካባቢው ነዋሪዎች እመት አይጠግቤን የሚቀርቦቸውም ሆነ ቤታቸው የሚገባ ማንም ሰው የለም፡፡ መኖሪያቸውን የማውቀው እኔ ብቻ ነኝ፡፡ መንገድ ላይ እን ሳገኛቸው ሰው ወዳጁ አባ ይጠይቁኝ እንጂ እቤት አይመጡም እንዴ ! ኃጢአቴ እኮ በዛ፤ ይፍቱኝ ጠበልም ይርጩኝ ብለው መስቀል ተሳልመው ይሄዳሉ፡፡
     ዐብይ ጾም ሊገባ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ሌሊት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሄድ መሀል መንገድ ላይ ብቻቸውን ቆመው ቸው፡፡ ሰውነታቸው በጣም ከስቶ ሥጋቸው አልቆአል፡፡ የለበሱት ቀሚስ እላያቸው ብጭቅጭቅ ብሎአል ፡፡ ጠጉራቸው ተንጨባል፤ በፍጥነት ወደ እኔ መጡ፤ ነገሩን በትኩረት እየተከታተልኩ እንደምን አደሩ እሜቴ አልቸው፤ እሳቸውም ድክም ባለ ቃል አዝነው አሞኝ ሰንበተ እኮ! በጣም አመመኝ ! ” አሉ ወዲያው በፍጥነት ከየት መጣ ሳይባል በቁጣ ቃል አባ የሰፈሩ ሰው ሁሉ ታማለች ልትሞት ደርሳለች እያለ ከበሮ ይደልቃል እኔ ግን አልሞትም !  እናተን ሁላችሁን ቀብሬ ሳልጨርስ አልሞትም እያሉ በመጮ ጥለውኝ በሩጫ ሄዱ፡፡
     አባ ዘመደ ብርሃን በዐብይ ምን የሚያሳልፉት በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሰለሆነ ለሁለት ወር አልነበሩም ፡፡ እመት አይጠግቤ አቅማቸው ደክሞ፣ ጉልበታቸው ዝሎ፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ዳኛ ተይዘው ይሰቃያሉ፡፡ በአጠገባቸው ቀድቶ የሚሰጣቸው፣ ምግብ አብስሎ የሚያቀምሳቸው ማንም የለም፡፡ በዚያ ሰፊ ግቢ ውስጥ ሻንቆ ብቻውን ያላዝናል፡፡ የሰፈሩ ሰው የእመት አይጠግቤን መጥፋት ቢያውቅም ይህች ጉድ እንደ ልማ መድኃኒት ስትቀምም ተደብቃ ይሆናል ብሎ ያወራል፡፡ ግን ቀናት፣ ሳምንታት ወራት አለፉ ፡፡ እመት አይጠገቤ ግን ከቤታቸው ብቅ ማለት አልቻሉም፡፡


 የመጨረሻዉ ክፍል ይቀጥላል




ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ