ከመጣብን ፈተና ምን አተረፍን ?
ጥር 14 ቀን ጠዋት የሰማነው ዜና የቤተክርስቲያን ፈተና ነበር፡፡ አይምጣብን አይባል ነገር ለብዙዎች ያልተጠበቀ የቤተክርስቲያን ሕልውና ላይ የተጋረጠ ፈተና፡፡ “ሳይደግስ አይጣልም ” እንዲሉ የነነዌ ሰዎች ጾም በመካከል በመኖሩ የመጣውን ፈተና ለማሽነፍ ማቅ ለብሰን እንባችን እንደ ጎርፍ እያወረድን የሐዘናችን ጥግ ለመግለጽ ጸጉራችንን ተላጭተን፣ ጥቁር ለብሰን “ አቤቱ አድነን ልንጠፋነው” ብለን ጮህን፡፡
ፈተናው ጠንክሮ ብዙዎች በአደባባይ አንድ ሲኖዶስ ብለው መሰከሩ፡፡ ቤተመቅደስ ተደፈረ ሰዎች ሞተው ሰማዕትነትን ተቋናጁ ደማቸውን አፈሰሱ ቆሰሉ፣ ታሰሩ ከቤተ-ክርስቲያን ጎን ቆሙ፡፡ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም የምስራች ሰማን፤ የሐዘናችን ደመና ተገፎ ፀሐይ ወጣ ችግሩ በሰላም ተፈታ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሳትከፋፈል በአንድነቷ ፀናች፡፡
ይህ ፈተና የመጣው ለምን ይሆን ? አንድም ለቅጣት፣ አንድም ለትምህርት ብቻ ስለ ብዙ ምክንያት ነው ብለን እንለፈው፡፡ በመጣብን ታላቅ ፈተና ምን ትምህርት ወስደን ? ምንስ ትርፍ አግኝተን ይሆን? የእኔ ጥያቄ ነው፡፡
አዎ በቤተክርስቲያን ላይ በመጣው ፈተና ምን አተረፍን ? ምን ፀጋና በረከት አገኘን ? እንወያይበት፡፡
ኢትዮጵያ ሀገራችን በዚህ ፈተና ምን አተረፈች?
ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ-ክርስቲያን ምን አተረፈች?
ቅዱስ ሲኖዶስ እና ቋሚ ሲኖዶስ ምን አተረፉ?
ጠቅላይ ቤተ-ክህነት ምን አተረፈ?
እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ምን አተረፈ?
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ምን አተረፉ?
በሀገር ውስጥም በውጭውም ሀገር ያሉ አገልጋዮች ምን አተረፉ?
እያንዳንዱ ክርስቲያንስ በግል መንፈሳዊ ሕይወቱ ምን አትርፎበት ይሆን?
ሃይማኖታቸው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያልሆኑ ሰዎችስ ይህን ፈተና አይተው ሰምተው ምን አትርፈውበት ይሆን ? እንወያይበት!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ