ሰኞ 3 ኦገስት 2026

ዋናው ገጽ

 

ማዕዶት ወደ መንፈሳዊነት፡፡

+++

ወደዚህ የሕይወት ትምህርት መድረክ እንኳን በደህና መጣችሁ፤

ማዕዶት፡- ወደ መንፈሳዊነት አብረን እንሻገር!"

 

"ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ "  ትንቢተ ዳንኤል 12÷3

በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ "ማዕዶት" የሚለው ቃል ትርጉም መሸጋገር ማለት ነው፡፡ ከኃጢአት ጨለማ ወደ ክርስቶስ ብርሃን የምናደርገው መንፈሳዊ ጉዞ ነው። በዚህ ገጽ ላይ የሚቀርቡት ትምህርቶች በፅንሰ-ሃሳብ ላይ ብቻ የተገደቡ ሳይሆኑ፣ በጾም፣ በጸሎትና በንስሐ የታጀበ "ተግባራዊ ክርስቲያናዊ ሕይወት" እንዴት መኖር እንደምንችል የሚያሳዩ ናቸው።

 

እነዚህን ትምህርቶች ስታነቡና በሕይወታችሁ ስትተገብሯቸው፣ በሃሳቡ ልዕልና ከመሬታዊው ጭንቀት ወደ ሰማያዊው ሰላም ትሻገራላችሁ። የእግዚአብሔር ቃልና የአባቶቻችን ምክር ልክ እንደ ብርሃን ፋኖስ እየመራችሁ፣ በሥራችሁ፣ በትዳራችሁና በማህበራዊ ግንኙነታችሁ ሁሉ ውስጥ ክርስቲያናዊ ምግባርን እንዴት መላበስ እንደምትችሉ ታውቃላችሁ።

 

በዚህ የመሸጋገር ገጽ ላይ በሃይማኖት ጸንቶ፣ በምግባር አጊጦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የምናደርገው የጋራ ጉዟችን ነው። እዚህ የሚለጠፉትን ትምህርቶች ልባችሁን ከፍ አድርጋችሁ ስትከታተሉ፣ ቅዱስ ጳውሎስ « ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።» ኤፌ 422-24 እንዳለው፤ በሃሳብ ልዕልና እየተሻገራችሁ አሮጌውን ሰውነት አውልቃችሁ አዲሱን መንፈሳዊ ማንነት ትለብሳላችሁ።

ወደዚህ የሕይወት ትምህርት መድረክ እንኳን በደህና መጣችሁ፤

ማዕዶት ወደ መንፈሳዊነት አብረን እንሻገር!"

 

መምህር ያዕቆብ ሰንደቁ

ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን

አዲስ አበባ

 

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ዋናው ገጽ

  ማዕዶት ወደ መንፈሳዊነት፡፡ +++ ወደዚህ የሕይወት ትምህርት መድረክ እንኳን በደህና መጣችሁ፤ ማዕዶት ፡- ወደ መንፈሳዊነት አብረን እንሻገር!"   " ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀ...