-->

ማዕዶት የያዕቆብ ሰንደቁ የጡመራ ገጽ

ማዕዶት የያዕቆብ ሰንደቁ የጡመራ ገጽ

ማዕዶት የያዕቆብ ሰንደቁ የጡመራ ገጽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን እና የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ሰባኪ እና መምህር የሆነው የያዕቆብ ሰንደቁ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ወጎች የሚፃፉበት ገጽ ነው፡፡ የዚህ የጡመራ ገጽ ዓላማም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ሁሉ ወደ ጽድቅ ወደ መልካም ሥነምግባር እንዲመለሱ ማስተማር ነው፡፡ “ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ፡፡” ትንቢተ ዳንኤል 12÷3

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጣዊ ክፍል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታ የፀሐይ መውጫ የተረጋጋ መንፈሳዊ መንገድ
አዲስ ገጽ

አንቀጸ ወራዙት/ወጣቶች/-"የቢራ ጎርፍ"

ገጹን ይመልከቱ

ወግ - ክንፍ አልባ ወፍ

 ክንፍ አልባ ወፍ

ያዕቆብ ሰንደቁ

ወዳጆቼአሁን ያለንበት የተቀደሰው የአቢይ ጾም ወቅት ከምግብ መከልከል ባለፈ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት እውነተኛ መንፈሳዊ ጉዞ ነው። ነገር ግን ጸሎት ከሌለው ጾማችን መሬት ላይ እንደሚንፈራገጥ፣ መብረር እንደማይችል ወፍ ይሆንብናል።

ጸሎት እንደ "መንፈሳዊ ክንፍ"

ታላቁ አባት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎትን "መንፈሳዊ ክንፍይለዋል። "ሰው ሳይጸልይ መዋል ማለት ክንፍ የሌለው ወፍ ለመብረር እንደሚሞክር ነውይላል። ጸሎት ከዚህ ዓለም የመሬት ስበት (ከጭንቀትና ከምኞትአውጥቶ ወደ መለኮታዊው ዓለም ያደርሰናል።

ቅዱስ ኤፍሬም ጸሎትን "ከከንፈር" ይልቅ "ከአንጀት" እንዲሆን ያደረገ ታላቅ አባት ነው። "የሕይወቴ ጌታና ሹም ሆይየሥራ ፈትነትን፣ የልብ መሰላቸትን፣ የሥልጣን መውደድንና የከንቱ ንግግርን መንፈስ አትስጠኝ። ይልቁንም የንጽሕናን፣ የትሕትናን፣ የትዕግሥትንና የፍቅርን መንፈስ ለእኔ ለባሪያህ ስጠኝ።በማለት ይጸልያል፡፡

ቅዱስ አትናቴዎስ እንደሚነግረን፣ መዝሙረ ዳዊት መፀለ የነፍሳችን መስታወት ነው በማለት ይገልጸዋል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ "ወደ ማርሴሊኖስ በተላከ መልእክትላይ እንደሚነግረን፣ መዝሙረ ዳዊት ከሌሎች መጽሐፍት ልዩ የሚያደርገው የሰውን ልጅ ውስጣዊ ማንነት የሚገልጥ በመሆኑ ነው። ሌሎች መጽሐፍት የታሪክ ክስተቶችን ሲነግሩን፣ መዝሙረ ዳዊት ግን የራሳችንን ስሜትና ሕይወት በቃለ እግዚአብሔር ውስጥ እንድናገኝ ያደርገናል።

መዝሙራትን ስናነብና ስንጸልይ የዳዊትን ቃላት ብቻ አንደግምም፤ ይልቁንም ቃላቱን እንደ ራሳችን ቃላት አድርገን እንድንጸልይ ይረዱናል። ለምሳሌም በጠላቶች ስንከበብ (መዝ. 3) በኃጢአት ተጸጽተን ይቅርታ ስንሻ (መዝ. 50/51) ወይም እግዚአብሔርን ማመስገን ስንፈልግ (መዝ. 102) እንደ መድኃኒት እንጠቀምባቸዋለን ይላል።

ጸሎት በየትኛውም ቦታና ሰዓት

ብዙዎቻችን ጸሎት የሚቻለው ቤተ ክርስቲያን ተንበርክከን ብቻ ወይም ጸጥ ባለ መንፈሳዊ ሥፍራ ብቻ ይመስለናል። ነገር ግን እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት፣ ጸሎት ቦታና ጊዜ አይገድበውም። በሥራ ገበታህ፣ በመንገድ ላይ ወይም በቤት ውስጥ ሆነህ ልብህን ወደ ሰማይ በማንሳት ከፈጣሪህ ጋር መነጋገር ትችላለህ በማለት ያስተምራል። ጸሎት በአንደበት የሚደገም ቃል ብቻ ሳይሆን፣ በልብ የሚደረግ ምስጢራዊ ንግግር ነው ሲል ይገልጻል፡፡

ንባብና ጸሎት፦ ቅዱስ ጀሩም እንደገለጸው "ስትጸልይ አንተ እግዚአብሔርን ታናግረዋለህ፤ መጽሐፍ ስታነብ ደግሞ እርሱ ያናግርሃል" ጸሎታችን የአእምሮ ሰላም እንዲሰጠን መጽሐፍትን በማንበብ ልባችንን ማነቃቃት ይኖርብናል። መጽሐፍትን ማንበብ ለጸሎታችን እንደ ነዳጅ ነው፤ ጸሎታችን እንዲያርግና ወደ እግዚአብሔር ዙፋን እንዲደርስ ያደርገዋል።

 ጸሎት እንደ "መንፈሳዊ መድኃኒት ቤት ነውበዚህ በጭንቀትና ሩጫ በሞላበት ዓለም ውስጥ አእምሯችን ሰላም የሚያገኘው በጸሎት ነው። ቅዱስ አትናቴዎስ መዝሙራትን እንደ "መንፈሳዊ መድኃኒት ቤት " ይቆጥራቸዋል። ለማንኛውም የአእምሮ ጭንቀትና የነፍስ መታወክ የሚሆን ፈውስ በመዝሙራትና በጸሎት ውስጥ ይገኛል። ጸሎት ነፍሳችንን የሚያረጋጋ ወደብ፣ አእምሯችንንም ከዓለማዊ ማዕበል የሚጠብቅ መልሕቅ ነው።

አንባቢያን ሆይበዚህ በተቀደሰ የዓቢይ ጾም ወቅት ጸሎትን የዕለት ተዕለት እስትንፋሳችን እናድርገው። እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ ምክር መዝሙረ ዳዊትን እንደ መስታወት እንጠቀምበት። በአንደበት ብቻ ሳይሆን በልብ፣ በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ቦታ ሆነን ወደ ፈጣሪያችን እንጮህ። እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎትን "መንፈሳዊ ክንፍ አድርገን በጸሎት ኃይል ወደ ሰማያዊ ሕይወት እንክነፍ።

መጽሐፍትን በማንበብና በመጸለይ የምናገኘው ሰላም ከማንኛውም ምድራዊ ደስታ በላይ መሆኑን በተግባር የምናይበት ጾም ይሁንልን።

"መዝሙረ ዳዊት እንደ ገነት ነው፤ በውስጡም የሌሎቹ መጽሐፍት ፍሬዎች ሁሉ ይገኙበታል።" — ቅዱስ አትናቴዎስ

 

ያዕቆብ ሰንደቁ

እሁድ ዘወረደ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ/ም

 አዲስ አበባ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ማዕዶት አንቀጸ ወራዙት እና የወጣቶች ተግባራዊ ክርስቲያናዊ ሕይወት

ማዕዶት፡- ወደ መንፈሳዊነት አብረን እንሻገር! "ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት  ለዘላለም ይደምቃሉ"  (ትንቢተ ዳንኤል 12÷3) በቤተክርስቲያናችን...

በመምህር ያዕቆብ ሰንደቁ የተዘጋጀ መንፈሳዊ መፃሕፍት

Image 1
Image 2
Image 3
Image 4

የሳምንቱ የመፅሐፍ ቂዱስ ጥቅስ

"በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም መንገድህን ያቀናልሃል።" ምሳሌ 3፡5-6

Video