-->

ማዕዶት የያዕቆብ ሰንደቁ የጡመራ ገጽ

ማዕዶት የያዕቆብ ሰንደቁ የጡመራ ገጽ

ማዕዶት የያዕቆብ ሰንደቁ የጡመራ ገጽ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን እና የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ሰባኪ እና መምህር የሆነው የያዕቆብ ሰንደቁ መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ወጎች የሚፃፉበት ገጽ ነው፡፡ የዚህ የጡመራ ገጽ ዓላማም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ሁሉ ወደ ጽድቅ ወደ መልካም ሥነምግባር እንዲመለሱ ማስተማር ነው፡፡ “ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ፡፡” ትንቢተ ዳንኤል 12÷3

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጣዊ ክፍል የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታ የፀሐይ መውጫ የተረጋጋ መንፈሳዊ መንገድ
አዲስ ገጽ

አንቀጸ ወራዙት/ወጣቶች/-"የቢራ ጎርፍ"

ገጹን ይመልከቱ

ወግ - «ማራናታ - ጌታችን ሆይ

 

                                               

 


 

 «ማራናታ - ጌታችን ሆይ፣ » 1ኛ .ቆሮንቶስ16፥22  

 በያዕቆብ ሰንደቁ 

መስከረም 7 ቀን 2019 ዓ.ም 

ምዕራፍ  አንድ

 

በዋሺንግተን ዲስ ከተማ ወርሃ መስከረም ፣ የበጋው አየር ተለውጦ ደስ የሚል የመኸር ቅዝቃዜ አካባቢውን ይሸፍነዋል። በየመንገዱ ዳር ያሉ ግዙፍ ዛፎች አረንጓዴ ቅጠሎቻቸውን ወደ ወርቃማ፣ ብርቱካናማና ቀይ ቀለም ቀይረው፣ በነፋሱ እየተወዛወዙ በቀያዮቹ የጡብ አስፋልቶች ላይ ረጋ እያሉ ይረግፋሉ። በዚህች አሜሪካዊት ከተማ እምብርት በሚገኘው ዝነኛው ዘጠነኛው ጎዳና (9th and U Street) ሲራመዱ ግን፣ አየሩ በአዲስ አበባ ፒያሳ ወይም ቦሌ ድባብ የተሞላ ይመስላል። በግዕዝ ፊደላት ከተጻፉት የንግድ መደብሮችና ምግብ ቤቶች ደጅ የሚወጣው የሚቆላ ቡና ጢስ እና የቅመም ጠረን አየሩን ሲያውደው፣ ከየአቅጣጫው የሚሰማው የአማርኛና የትግርኛ ወግ መንገዱን በሞቅ ያለ የሀገር ቤት ስሜት ይሞላዋል።

 

በዚህ ውብ እና ቀለማቱ ባሸበረቀው የዲሲ ጎዳና ላይ ሳታቋርጥ በፈገግታና በሞቅ ያለ ሰላምታ የምትጓዘው ሜሪ፣ በውጫዊ ገጽታዋ የዘመናዊዋን ዋሺንግተን ዲሲ ሕይወት ሙሉ በሙሉ የተላበሰች ትመስላለች። 10 ዓመት ሕፃንነቷ ወደ አሜሪካ የመጣችው ሜሪ፣ ዛሬ 30 ዓመቷ በከፍተኛ የሕግ ሙያ የተሰማራች፣ ስኬታማና ጥሩ ደሞዝ ያላት ጠንካራ ሴት ናት። ጽዱ አለባበሷ፣ በራስ መተማመን የተሞላው አካሄዷ እና የሚያበራው ውበቷ አሜሪካዊቷን የሕግ ባለሙያ ቢያንጸባርቅም፣ ከዚህ ዘመናዊ ሽፋን ስር ግን ፍጹም የተለየና ለሀገሯ መንፈሳዊነት የሚራብ ጥልቅ ውስጣዊ ማንነት ተሸሽጓል።

 

ሜሪ በዲሲ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እና በቤተክርስቲያኑ አጸድ ውስጥ በሁሉም ዘንድ እጅግ የተወደደች እና የተከበረች እናት ናት። ከባለቤቷ ጋር የገነባችው የሞቀ ትዳር እና የሁለት ልጆቿ እናት መሆኗ፣ ለሌሎች አርአያ ናት እሁድ እሁድ ከቤተሰቧ ጋር ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጣ ፊቷ ላይ የሚታየው ቅንነትና አክብሮት፣ እንዲሁም ከታናሽ እስከ ታላቅ ለሁሉም የምትሰጠው ፍቅር ማህበረሰቡ እንደ እህትና እንደ ልጅ አቅፎ እንዲይዛት አድርጎታል።

 

ከሁሉም በላይ ግን የሜሪ ልዩ ምስጢር የሚገለጠው በሌሊቱ የቤተክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ ላይ ነው። እግዚአብሔር የቸራትን ማራኪና ልብ የሚነካ ድምፅ ይዛ በቤተመቅደስ ውስጥ ቁማ የሌሊቱን "ሰዓታት" ተቀብላ ስትል ድምጿ የምዕመኑን ልብ ወደ ሌላ መንፈሳዊ ዓለም የማሸጋገር ያህል ረቂቅ አቅም አለው። በቀን የሕግ መዛግብትንና የሙያ ውጥረትን የምትወጣው ሜሪ፣ ምሽት ላይ በቀጥታ መስመር የሚሰጠውን የኢትዮጵያ የአብነት ትምህርት ከየኔታ በትጋት ትከታተላለች፤ ይህ መንፈሳዊ ጥማቷ ነው በዲሲ ዘመናዊ ኑሮ ውስጥ የልቧን እርካታ የሚሰጣት እንዲህ ያለው መንፈሳዊ እሴት ነው።

 

አሁን ግን በዚህች መንፈሳዊና ስኬታማ ሴት ህይወት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ሊከፈት ነው። አሜሪካ ገብታ 10 ዓመት ልጅነቷን ከተሰናበተች 20 ረጅም ዓመታት በኋላ፣ ወደ ተወለደችበት ሀገሯ ኢትዮጵያ ለመመለስ የመጨረሻ ዝግጅቷን እያደረገች ትገኛለች። በዲሲ ቤቷ ሳሎን ውስጥ የተዘረጉትን ትላልቅ ሻንጣዎች እያስተካከለች፣ ለሀገር ቤት ዘመዶቿ የሚሆኑ ስጦታዎችን ስታዘጋጅ፣ አእምሮዋ በናፍቆትና በትዝታ ንፋስ ይወዛወዛል።

 

የሻንጣዋን ዚፕ ስትዘጋና መስኮቷን ከፍታ የዲሲን የመኸር አየር ስትተነፍስ፣ በፊቷ ላይ የሚታየው ፈገግታ ከበፊቱ የበለጠ ደስተኛነቷን ይመሰክራል፡፡  በህፃንነቷ የተለየቻትን ሀገር፣ ዛሬ 30 ዓመቷ ሙሉ ሴት፣ እናት፣ ስኬታማ የሕግ ባለሙያ እና መንፈሳዊ ሰው ሆና ልትጎበኛት ስትዘጋጅ፣ በዋሺንግተን ዲሲ እና በአዲስ አበባ መካከል ያለው የናፍቆት ድልድይ ሙሉ በሙሉ የተገነባ ይመስላል።

 

     ምዕራፍ 2 *****

 

ከረጅም ዘመናት የተስፋና የናፍቆት ጥበቃ በኋላ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ፣ እንግዳ መቀበያው አዳራሽ በሰውና በስሜት ተጨናንቆ ነበር። ከዓመታት በኋላ የሀገሯን አየር ስትተነፍስ ልቧ በደስታ መታ እርሷን ለመቀበል በእድሜ የገፉት አያቷ እጆቻቸውን ዘርግተው በግንባሯ ላይ ሲስሟት ግን የስሜቷ ማዕበል ከቁጥጥር ውጭ ሆነ። በታዋቂው ቢጫ ታክሲ ተሳፍረው ወደ ሳርቤት አካባቢ ወደሚገኘው የአያቷ ቤት በሚያመሩበት መንገድ ላይ፣ የሜሪ ዓይኖች ከታክሲው መስኮት አልራቁም። የሕፃንነት ትዝታዋ ያረፈበት ሰፈር ሙሉ በሙሉ ተለዋውጧል፤ የተገነቡት አዳዲስ ሕንፃዎች፣ የተለወጡት መንገዶች፣ እና በየመንገዱ ዳር የሚታዩት የሕይወት ውጣ ውረድ ያጎሳቆላቸው የሰፈሯ ሰዎች ገጽታ ስታይ ልቧን ሀዘን ነካው።

 

ወደ ሀገሯ ተመልሳ በገባች በሳምንታት ውስጥ የአያቷ ቤት በዘመድ አዝማድና በወዳጅ ተሞላ። "እንኳን ደህና መጣሽ" የሚለው ሞቅ ያለ ሰላምታ፣ የቡናው ጠረን እና የዱሮ ትዝታ ወግ ለቀናት ቢቀጥልም፣ አሥራ አምስት ቀናት ሙሉ ቤተሰቦቿንና እንግዶችን በማስተናገድ ከረመች። በዚህ መካከል ወንድሞቿና የአጎቷ ልጆች "በምሽት ወጥተን ከተማዋን እናስጎብኝሽ፣ የባህል ቤቶችን እናሳይሽ" የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ያቀርቡላት ጀመር። በዋሺንግተን ዲሲ ለዘፈንና ለጭፈራ ልቧ ዝግ ሆኖ፣ መንፈሳዊ ሕይወትንና ቤተክርስቲያንን ብቻ ስታዘወትር የኖረችው ሜሪ፣ በውሳኔዋ ብዙ አልተደሰተችም። ነገር ግን "ይህች ምን ዓይነት ችጋራም ናት! እናዝናናት ባልናት እምቢ ትላለች" ብለው እንዳይታዘቧት በመስጋት፣ ፈራ ተባ እያለች በአንድ ቅዳሜ ምሽት ከእነርሱ ጋር ለመሄድ ወሰነች።

 

የመጀመሪያው ያረፉበት ቦታ ጸጥታ የሰፈነበት፣ የሀገር ቤት ውበትና ባህል የሚንጸባረቅበት የባህል ቤት ነበር። በቦታው የቀረበው የክትፎ  የጠጁ አቀራረቡና ጣዕም ልዩ በመሆኑ፣ ሜሪ ከተዘጋጀው ጠጅ ጥቂት ቀመሰች። ከመንፈሳዊ ህይወቷ ወጥታ በለመደችው የጸጥታ መንፈስ ውስጥ ሳለች፣ ያች ጥቂት የቀመሰቻት ጠጅ አእምሮዋን ብዥ ሰውነቷን ትንሽ ሞቅ አደረገቻት። ሆኖም እኩለ ሌሊት ሲሆን፣ ከእርሷ ጋር የነበሩት ወንድሞቿ "ቦታ እንቀይር" በማለት እርሷ የማታውቀውን ሌላ የባህል ቤት ይዘዋት አመሩ።

 

ሁለተኛው ቤት ሲገቡ ግን ድባቡ ሙሉ በሙሉ የተቀየረ ነበር። ቤቱ በጩኸት፣ በዘፈንና በአዝማሪ ድምፅ የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብረዋት የነበሩት ወንድሞቿ በመጠጥ ብዛት ሰክረው የሚሰሩትን ማወቅ አቅቷቸዋል። በውስጡ ያለው አብዛኛው ሰው በስሜትና በአልኮል ናውዞ የሚገኝ ሲሆን፣ የአዝማሪው ግጥሞች ጸያፍና ነውረኛ ነበሩ። በየጥጋጥጉ ወንዶችና ሴቶች ያለ አንዳች እፍረት ነውረኛ ድርጊት ሲፈጽሙ፣ አንዳንዶቹም ልብሳቸውን ጥለው እንደ አበደ ሰው እርቃናቸውን ይጨፍራሉ ሲጋራ፣ ሀሺሽና አልኮል በሕግ የተፈቀደ ይመስል በየቦታው ይጨስና ይጠጣል። ይባስ ብለው ወንድሞቿ ሜሪን ከመካከላቸው አስገብተው እንድትጨፍር፣ መጠጥ እንድትጠጣና እስክስታ እንድትወርድ ይገፋፏት ጀመር።

 

በዚህ ሁሉ ነውር መካከል የተቀመጠችው ሜሪ፣ ጭንቀቷና ድንጋጤዋ ወሰን አጣ። "በዋሺንግተን ዲሲ ይህን ያህል ዘመን ስኖር አንድ ቀን እንኳ ጭፈራ ቤት ሄጄ አምሽቼ የማላውቅ ሴት፣ ዛሬ በገዛ ሀገሬ እቀደሳለው ብዬ መጥቼ እንዲህ ባለው የኃጢአት ጉድጓድ ውስጥ ተገኘሁ" በማለት ራሷን እጅግ አድርጋ ትወቅስ ጀመር። ወንድሞቿ በመጠጡ ብዛት ቦታውን ለቀው ለመሄድ ፍቃደኛ ባይሆኑም፣ ሜሪ በዕንባ በተቀላቀለ ልመናና  ከሌሊቱ አሥር ሰዓት ተኩል ገደማ ወደ ቤታቸው እንዲወስዷት አደረገች።

 

በማግስቱ ዕለተ ሰንበት እንደመሆኑ መጠን፣ ሜሪ ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ቅዳሴ ልታስቀድስና አምላኳን ልታመሰግን አቅዳ ነበር። ይሁን እንጂ ሌሊቱን ሙሉ በዚያ ዓይነት የኃጢአትና የነውር ስፍራ ማሳለፏ የሕሊና እረፍት አጣች። የሰራችውን አላስፈላጊ ድርጊትና የወደቀችበትን የፈተና ሌሊት እያሰበች፣ በፈጣሪዋ ፊት በምሬት ተጸጸተች፤ የልቧ መንፈሳዊ ጥማትም ከቀደመው ይበልጥ በንስሐና በጸሎት ተጸጸተ። ከመቅረት ከ ነበደሌም ቢሆን ወደ ቤተክርስቲያን ልሂድ ብላ ነጠላዋን ለብሳ ወጣች፡፡

  

  ምዕራፍ ሦስት ******* 

በኢትዮጵያ የነበራት የሁለት ወር ከዐሥራ አምስት ቀን ቆይታ እንዳሰበችው መንፈሳዊ እርካታ ያገኘችበት አልነበረም። ጥንታውያኑንና ታሪካውያኑን የአክሱም ጽዮንን፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን፣ የፋሲል ግንብን፣ የጣና ቂርቆስ ገዳምን እንዲሁም በቅርብ የሚገኘውን የደብረ ሊባኖስ ገዳም የመሳለም ጥልቅ ፍላጎት ቢኖራትም፣


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ማዕዶት አንቀጸ ወራዙት እና የወጣቶች ተግባራዊ ክርስቲያናዊ ሕይወት

ማዕዶት፡- ወደ መንፈሳዊነት አብረን እንሻገር! "ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፥ ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት  ለዘላለም ይደምቃሉ"  (ትንቢተ ዳንኤል 12÷3) በቤተክርስቲያናችን...

በመምህር ያዕቆብ ሰንደቁ የተዘጋጀ መንፈሳዊ መፃሕፍት

Image 1
Image 2
Image 3
Image 4

የሳምንቱ የመፅሐፍ ቂዱስ ጥቅስ

"በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም መንገድህን ያቀናልሃል።" ምሳሌ 3፡5-6

Video